በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጠ/ሚ ሼንዞ አቤ በጤና ምክንያት ከሥልጣን እንደሚሰናበቱ አስታወቁ


የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ
የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ

የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ፣ በጤና ስጋት ምክንያት ከሥልጣን እንደሚሰናበቱ አስታውቀዋል። ወግ አጥባቂው ጠቅላይ ሚኒስትር፣ በቀጠናዊ ግንኙነት ላይ ድብልቅ ስኬት ማግኝታቸው ተዘግቧል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትናንት ቶክዮ ሆነው፣ በቴሌቪዥን ባደረጉት ጋዜጣዊ ጉባኤ፣ ህክምና ላይ ሆኜ፣ ሥራየን ማከናወን አልችልም ብለዋል። ሆድ እቃቸው ላይ በየጊዜው የሚያገረሹ ቁስሎች እንዳሉባቸው ጠቁመዋል።

የ65 ዓመት እድሜው ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ለስምንት ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ ነው ሥልጣን ላይ የቆዩት። ጃፓን ውስጥ ለዚህ ያህል ርዝመት ሥልጣን ላይ ለመቆየት፣ የመጀመያው ጠቅላይ ሚኒስትር ናቸው ተብሏል። የሥልጣን ጊዜያቸው በመጪው ዓመት ነበር የሚያበቃው።

XS
SM
MD
LG