በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጃፓን፣ ዩናይትድ ስቴትስና ደቡብ ኮሪያ ዲፕሎማቶች ሰሜን ኮሪያ ላይ አበሩ


በዩናይትድ ስቴትስ የሰሜን ኮሪያ ጉዳዮች ልዩ መልዕክተኛ ሱንግ ኪም፣ በጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የጃፓን የእስያና የኦሺኒያ ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር ታኪሮ ፈናኮሺ፣ እንዲሁም የደቡብ ኮሪያ ልሳነ ምድርና የደህንነት ጉዳዮች ተወካይ ኪም ገን
በዩናይትድ ስቴትስ የሰሜን ኮሪያ ጉዳዮች ልዩ መልዕክተኛ ሱንግ ኪም፣ በጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የጃፓን የእስያና የኦሺኒያ ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር ታኪሮ ፈናኮሺ፣ እንዲሁም የደቡብ ኮሪያ ልሳነ ምድርና የደህንነት ጉዳዮች ተወካይ ኪም ገን

ከሰሜን ኮሪያ ሊመጣ የሚችለውን አዲሱን የኒውከለር ጦር መሳሪያ ሙከራ ጨምሮ የሚመጣውን ማናቸውንም ጥቃት በጋራ ለመመከት እንደሚሰሩ የዩናይትድ ስቴትስ፣ ጃፓን እና ደቡብ ኮሪያ ዲፕሎማቶች ያላቸውን ቁርጠርኝነት በድጋሚ ማረጋገጣቸውን ዛሬ አስታወቁ፡፡

በሰሜን ኮሪያ ጉዳይ ኃላፊነት ያለባቸው ሦስቱ ከፍተኛ ዲፕሎማቶች የደህንነት ህብረታቸውን ለማጠናከር መስማማታቸውንም አሶሴይትድ ፕሬስ ከጃፓን ዘግቧል፡፡

ጃፓንና ደቡብ ኮሪያ በመከካላቸው ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነትን ጨምሮ የሶስትዮሹን ግንኙነት ማጠናከር እንደሚኖርባቸው መስማማታቸው በዘገባው ተመልክቷል፡፡

ጃፓን በደቡቡ ኮሪያ ልሳነ ምድር ከነበራት ቅዥ ግዛት ጋር በተያያዘ ታሪካዊ ውዝግብ በደቡብ ኮሪያና ጃፓን መካከል ያለው ግንኙነት ሻክሮ መቆየቱን ዘገባው አስታውሷል፡፡

ሦስቱ ዲሎማቶች በዩናይትድ ስቴትስ የሰሜን ኮሪያ ጉዳዮች ልዩ መልዕክተኛ ሱንግ ኪም፣ በጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የጃፓን የእስያና የኦሺኒያ ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር ታኪሮ ፈናኮሺ፣ እንዲሁም የደቡብ ኮሪያ ልሳነ ምድርና የደህንነት ጉዳዮች ተወካይ ኪም ገን መሆናቸው ተዘግቧል፡፡

XS
SM
MD
LG