በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጃፓን የእንቅስቃሴ ክልከላ ማንሳት ጀመረች


የቶኪዮ ኦሊምፒክስ ተቃረበ፥ ጃፓን የዋና ከተማዋን የኮቪድ-19 የእንቅስቃሴ ክልከላ ቀስ በቀስ ማንሳት ጀምራለች።

በሚቀጥለው ሃምሌ ወር በሚከፈተው የቶኪዮ ኦሊምፒክስ እየተቃረበ ባለበት ባሁኑ ወቅት የጃፓን መንግሥት በዋና ከተማዋ እና በሌሎችም የሀገሪቱ አካባቢዎች ኮቪድ-19ን ለመከላከል ጸንቶ የከረመውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቀስ በቀስ ለማንሳት ያለውን እቅድ ዛሬ ይፋ አደረገ።

የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ዮሽዴ ሱጋ በሰጡት መግለጫ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የፊታችን ዕሁድ ሲበቃ ወደ ከፊል የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ እናመራለን ብለዋል። ቀለል የሚለው መመሪያም ከዕሁድ በኋላ ይጀምርና እስከቶኪዮ ኦሊምፒክስ መክፈቻ በሚኖሩት አስራ ሁለት ቀናት ይቀጥላል። ከዝህም በተጨማሪ የጃፓን መንግሥት የኦሊምፒክስ ነክ ዝግጅቶች ላይ እስከ 10 000 የሚሆኑ ተመልካቾች እንዲገቡ እንደሚፈቅድ ያስታውቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የጀርመኑ የመድሃኒት ኩባኒያ ኪዩርቫክ የቀመመው የኮቪድ-19 ክትባት ላይ ብዛት ባላቸው ተሳታፊዎች ላይ የተካሄደው የኋለኛ ምዕራፍ ሙከራ እንዳንድ አዎንታዊ ያልሆኑ ውጤቶች ማስየቱ ተገለጸ። የክትትሉ ቅድመ ውጤት እንዳሳየው ክትባቱ ቫይረሱን በ47 ከመቶ ብቻ የመከላከል ዐቅም አሳይቷል፣ የዓለም የጤና ድርጅት ባወጣው መስፈርት የሚሰራ ክትባት ቢያንስ ሃምሳ ከመቶ የመከላከል አቅም ሊያሳይ ይገባል።

የመድሃኒት ኩባኒያው ሃላፊዎች ሙከራዎቹ ጥሩ ውጤት ላያመጣ የቻለው ከመጀመሪያው በኋላ በተቀሰቀሱት አዳዲስ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ዓይነቶች ምክንያት እንደሆነ ይናገራሉ።

XS
SM
MD
LG