በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ምርጫውን ያሸነፉት የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር በፖሊሲያቸው ጠንክረዋል


የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ
የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ

ባልተጠበቀው የምርጫ ውጤት ከፍተኛ ድል የቀናቸውና የተበረታቱት የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ፣ ዛሬ ሰኞ ባሰሙት ንግግር፣ ቻይናን ለመቋቋም የሚያስችል የመከላከል ፖሊሲ ላይ እንደሚያተኩሩ፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለማገገም አጠንክረው እንደሚሰሩ ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡

የኪሺዳ ወግ አጥባቂው ሊብራል ዴሞክራቲ ፓርቲ፣ በትናንቱ ምርጫ ምክር ቤቱን በብቸኝነት መቆጣጠር የሚያስችለውን መቀመጫ አግኝቷል፡፡

ይህ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተከፋፈለውን ፓርቲያቸውን ለመቆጣጠርም ሆነ በምክር ቤቱ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለማገገምም ተጨማሪ በጀት ማሳለፍን ጨምሮ አጀንዳዎቻቸውን በቀላሉ ለማሳለፍ ነጻ መንገድ እንደሚከፍትላቸው ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG