በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጃፓን ወታደራዊ ወጭዋን በከፍተኛ ደረጃ እንደምታሳድግ አስታወቀች


ከ200ሺ ጃፓናውያን በላይ የሞቱበትን የሄሮሺማና ናጋሳኪው የኒዩክለር ቦምብ ጥቃት የተፈጸመበትን እለ በሞቶያሱ ወንዝ ላይ በወረቀት የተጠቀለሉ ፋኖሶችን ለኩሰዋል፤ እአአ ነሐሴ 6/2022
ከ200ሺ ጃፓናውያን በላይ የሞቱበትን የሄሮሺማና ናጋሳኪው የኒዩክለር ቦምብ ጥቃት የተፈጸመበትን እለ በሞቶያሱ ወንዝ ላይ በወረቀት የተጠቀለሉ ፋኖሶችን ለኩሰዋል፤ እአአ ነሐሴ 6/2022

ጃፓን ለረጅም ጊዜ ታቅባ ከቆየችበት የወታደራዊ ኃይል ግንባታ እገዳ በመውጣት የመካላከያ ወጭዋን እንደምታሳድግ አስታወቀች፡፡

ጃፓን ከአስርት ዓመታት በኋላ ከዚህ ውሳኔ የደረሰችው ከቻይና በኩል በተሰነዘረባት ስጋት ሳቢያ መሆኑን አስታውቃለች፡፡

የሁለተኛው የዓለም ጦርነትን ወደ ፍጻሜ ያመጣውና ከ200ሺ ጃፓናውያን በላይ የሞቱበትን የሄሮሺማና ናጋሳኪው የኒዩክለር ቦምብ ጥቃት የተፈጸመበትን እለት በዚህ ወር ማክበሯም ተመልክቷል፡፡

ይሁን እንጅ ምንም እንኳ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ለዓለም ሰላም የሚሰሩ መሆኑን ቢገልጹም፣ እኤአ በ1945 ጃፓን ከተሸነፈችበት ጦርነት ወዲህ፣ አገራቸው የመከላከያ ወጭዋን በከፍተኛ ደረጃ እንደምታሳድግ አስታውቀዋል፡፡

በቅርቡ ታይዋንን በጎበኙት የዩናይትድ ስቴትስ አፈጉባኤ የተበሳጨችው ቻይና ባላፈው ሳምንት በታይዋን ዙሪያ የጦር ልምምድ በማድረግ በርካታ ሚሳዬሎችን መተኮሷ ተዘግቧል፡፡

አንዳንዶቹ ሚሳዬሎች በጃፓን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ተብለው በተከለሉ የባህር ክልሎች ማረፋቸውን የቻይና ወታደራዊ እንቅስቃሴ ያሰጋት ጃፓን አስታውቃለች፡፡

ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት ፍጻሜ በኋላ እኤአ በ1945 የወጣው የአገሪቱ ህግ መንግሥት "የጃፓን ህዝብ ጦርነትን እንደ አገሪቱ ሉዓላዊ መብት መመልክትን ለዘላዓለም ያስወግዳል" ቢልም የጦርነት ሥጋት ከባህር ደጇ እየተጠጋ መመምጣቱ ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG