በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጃፓን መርዝ ጥቃት አድርሶ ሰዎች የገደለው አምልኮ መሪ በስቅላት ተቀጣ

እኤአ 1995 ጃፓን ዋና ከተማ ቶኪዮ የምድር ውስጥ ባቡር ተሳፋሪዎች ላይ የሳሪን መርዝ ጥቃት አድርሶ ሰዎች የገደለው አምልኮ ቡድን መሪ ዛሬ በስቅላት መቀጣቱ ተሰማ።

እኤአ 1995 ጃፓን ዋና ከተማ ቶኪዮ የምድር ውስጥ ባቡር ተሳፋሪዎች ላይ የሳሪን መርዝ ጥቃት አድርሶ ሰዎች የገደለው አምልኮ ቡድን መሪ ዛሬ በስቅላት መቀጣቱ ተሰማ።

“ሾኮ አሳሃራ” በሚል ተለዋጭ ስም የሚጠራው ቺዞ ማትሱሞቶ ዛሬ መሰቀሉን የጃፓን መንግሥት ቃል አቀባይ አስታውቋል።

በዘገባዎች መሰረት ሌሎችም የዚሁ የምጽዓት ቀን አምልኮ በርካታ አባላት እንደተሰቀሉ ነው ዘገባዎች ያመለከቱት። ምን ያህል እንደሆኑ አልታወቀም።

ባለቤታቸው ከሃያ ሦስት ዓመታት በፊት በደረሰው በመርዝ ጥቃቱ የሞቱባቸው አንዲት ሴት ቅጣቱ ይህን ያህል ዘመን መዘግየቱ ያሳዝናል ብለዋል።

ቶኪዮን ባሽመደመዳት የመርዝ ጥቃት ከአሥራ ሁለት የሚበልጡ ሰዎች ሲሞቱ ከስድስት ሺህ የሚበልጡ ሰዎች እንደታመሙ ይታወሳል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG