ሩሲያ በዩክሬን ላይ ለወሰደችው እርምጃ አጸፋ የሚሆን መዓቀብ ጃፓን እና አውስትራሊያ እንደጣሉ ታውቋል። ሁለቱ ሀገራት ቀደም ብለው ውሳኔዎችን ያስተላለፉትን ዩናይትድ ስቴትስ፣ የአውሮፓ ህብረት፣ ካናዳ እና ጀርመንን ተቀላቅለዋል።
አውስትራሊያ ምንጊዜም በጉልበታቸው ከሚመኩት በተቃራኒ እንደምትቆም የተናገሩት የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስር ስካት ሞሪሰን
“ከሁሉም አጋሮቻችን ጋር በመሆን ሩሲያን እንጋፈጣለን!” ብለዋል። ተከታታይ ማዕቀቦች እንደሚጠበቁ እና ይሄም የሂደቱ ጅማሬ መሆኑን ተናግረዋል።
የአውስትራሊያ መዓቀብ በሩሲያ የጸጥታ ምክር ቤት አባላት ላይ ያነጣጠረ ሲሆን፣ ጃፓን በበኩሏ የተመረጡ የሩሲያ ዜጎች ሀብት እንዳይንቀሳቀስ፣ እና የሩሲያ ቦንድ ሽያጭ በግዛቷ እንዳይካሄድ ወስናለች።
የዩክሬን ውጭ ጉዳይ ፕሬዚደንት ዲሜትሮ ኩልባ፣ የሩሲያው ፕሬዚደንት ቭላድሚርን ተጨማሪ ቅጣት ለማስቆም ከዚህም ከረረ ያለ ማዕቀብ በአስቸኳይ እንዲጣል አሳስበዋል።
በትናንትናው ዕለት ለተወሰዱት እርምጃዎች ምስጋናቸውን ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትር
“አሁን ላይ ፑቲንን ለማስቆም ጫናው መጠናከር አለበት። ዛሬውኑ ኢኮኖሚው እና አጋሮቹ በብርቱ ሊመቱ ይገባል” ብለዋል።
የዩክሬን ጦር ዛሬ ረቡዕ ዕለት በሩሲያ በሚደገፉ በሉሃንስክ ቀጠና በሚገኙ ተገንጣዮች በተሰነዘረ ጥቃት አንድ የዩክሬን ወታደር እንደተገደለ እና ተጨማሪ ስድስት ሰዎች እንደተጎዱ አስታውቋል።