በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለሺንዞ አቤ የታቀደውን መንግሥታዊ ቀብር በመቃወም አዛውንቱ ራሳቸውን አቃጠሉ


የፖሊስ መኮንኖች እና የእሳት አደጋ ሠራተኞች ለሺንዞ አቤ የታቀደውን መንግሥታዊ ቀብር በመቃውም ራሳቸውን ያቃጠሉ ግለሰብ አካባቢ ተሰባስበው፤ ቶክዮ፣ ጃፓን
የፖሊስ መኮንኖች እና የእሳት አደጋ ሠራተኞች ለሺንዞ አቤ የታቀደውን መንግሥታዊ ቀብር በመቃውም ራሳቸውን ያቃጠሉ ግለሰብ አካባቢ ተሰባስበው፤ ቶክዮ፣ ጃፓን

የቀድሞ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ቀብር በመንግሥታዊ ሥነ ስርዓት ለመደረግ መታቀዱን በመቃወም አንድ የ70 ዓመት አዛውንት ዛሬ ራሳቸውን በእሳት አቃጥለዋል።

የሃገሪቱ ባለሥልጣናትና መገናኛ ብዙሃን እንዳሉት፤ በጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ደጃፍ ላይ ራሳቸውን ያቃጠሉት ግለሰብ በአብዛኛው ሰውነታቸው ላይ ጉዳት ቢደርስም፣ የአደጋ ሠራተኞች ሲያገኟቸው ግን እራሳቸውን ያውቁ ነበር።

ግለሰቡ ለፖሊስ በሰጡት ቃል ሆን ብለው ነዳጅ በሰውነታቸው ላይ በማርከፍከፍ እሳት እንደለኮሱ ተናግረዋል።

ጃፓንን ለረጅም ዘመን ያገለገሉት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ በደቡብ ኮሪያ በሚገኝ ‘ዩኒፊኬሽን ቸርች’ ከሚባል ቤተ ክርስቲያን ጋር ግንኙነት አላቸው ተብሎ የሚጠረጠሩ ሲሆን፣ ባለፈው ሐምሌ እርሳቸውን በጥይት ተኩሰው በመግደል የተጠረጠሩት ግለሰብ ወላጅ እናታቸው ገንዘባቸውን ሁሉ ለማጣታቸው ይህን ቤተክርስቲያን ምክንያት ያደርጋሉ።

እቤ በጃፓን ለረጅም ዘመን የገዛውን ለዘብተኛ ዲሞክራቲክ ፓርቲ የመሩ ሲሆን፣ ፓርቲውን በፓርላማ ከሚወክሉት ግማሽ የሚሆኑት አባላት በደቡብ ኮሪያ ከሚገኝው ‘ዩኒፊኬሽን ቸርች’ ከሚባል ቤተ ክርስቲያን ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ፓርቲው ከሰሞኑ አስታውቆ ነበር።

ይህ ከታወቀ በኋላ የህዝብ አስተያየት ቀስ በቀስ ‘አቤ መንግሥታዊ የቀብር ሥነ ስርዓት አይገባቸውም’ ወደሚል ሲያዘነብል፣ ለወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ የነበረውን ድጋፍም ሸርሽሯል።

“አቤ ያገለገሉበትን ረጅም ዘመንና በዓለም አቀፍ መድረክ ያላቸውን ተቀባይነት ግምት ውስጥ በማስገባት መንግሥታዊ የቀብር ሥነ ስርዓት ይገባቸዋል” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪሺዳ ይከላከላሉ።

የሺንዞ አቤ ቀብር በሚቀትለው ማክሰኞ የሚፈጸም ሲሆን፣ የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ካመላ ሃሪስን ጨምሮ 6 ሺህ የሚሆኑ ታዳሚዎች እንደሚገኙ ይጠበቃል።

XS
SM
MD
LG