በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኩዮቶ ጃፓን ከተማ በአንድ ስዕል ስቱድዮ በተነሳ እሳት የሰው ህይወት አለፈ


ኩዮቶ በተባለች የጃፓን ከተማ በአንድ የተንቀሳቃሽ ስዕል ስቱድዮ ውስጥ በተነሳ እሳት ቢያንስ 23 ሰዎች ሞተዋል ወይም እንደሞቱ ተገምቷል ሲሉ ባለስልጣኖች ተናግረዋል። እሳቱ ሆን ተብሎ የተለኮሰ ነው የሚል ጥርጣሪ አለ።

የእሳት አደጋ ሰራተኞች በገለጹት መሰረት 13 ሰዎች መሞታቸው ተረጋግጧል። የኪዮቶው የሲኒማ ኩባንያ በሚገኝበት በባለ ሦስት ፎቁ ህንፃ ከፍተኛው ወለልና ወደ ጣራው በሚያመሩት ደረጃዎች ላይ 10 ሰዎች ራሳቸውን ስተው ተገኝተዋል። ከ30 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ከባድ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል። አንዳንዶቹ በአስጊ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ።

ፖሊሶች እንደሚሉት እሳቱ የተነሳው አንድ ሰው ወደ ህንፃው ገብቶ አቀጣጣይ ፈሳሽ ካፈሰሰበት በኋላ ነው። ሰውየው በእሳት ሲያቀጣጥለው “ሙቱ” እያለ ይጮህ ነበር። እሳቱ ሲነሳ 70 የሚሆኑ ሰዎች ህንጻው ውስጥ እንደነበሩ ተገልጿል።

የተጠርጣሪው ሰው ዕድሜ 41 ነው ተብሏል። ቆስሎ ወደ ሆስፒታል እንደተወሰደ ታውቋል።

የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ በትዊተር መልዕክት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG