በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የገንዘቤ ዲባባ አሰልጣኝ በስፔይን አበረታች መድሃኒት በመስጠት ተጠርጥረው ታሰሩ


አሰልጣኝ ጀማ አደን
አሰልጣኝ ጀማ አደን

ኢትዮጵያን ጨምሮ የበርካታ አገሮች አትሌቶችን የሚያሰለጥኑት ጃማ አደን አበረታች መድሃኒት ለሯጮ በመስጠት ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለዋል። ከሚያሰጡኗቸው አትሌቶችም የደም ናሙና ተወስዷል።

የሁለት ጊዜ የዓለም የ1500 ሜትር የቤት ውስጥ ሩጫ ሻምፒዮን ገንዘቤ ዲባባን ጨምሮ ሌሎች በርካታ የዓለማችን ግሩም የመካከለኛ ርቀት ሯጮችን የሚያሰለጥኑት ጃማ አደን አበረታች መድሃኒት ለሯጮች በመስጠት ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ።

የስፔይን የፖሊስ ሃይል ስማቸውን ያልጠቀሷቸው ሌሎች ሁለት ሰዎችም በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሆነ ገልጿል።

የስፔይን ፖሊስ በቁጥጥር ስር ያዋላቸውን ሰዎች ስም ዝርዝር ይፋ አላደረገም። ሆኖም በስፔኗ ሳባዴል ከተማ በቁጥጥር አውለው ከወሰዷቸው ግለሰቦች መካከል አንዱ ጀማ አድን ናቸው። አሰልጣኝ አደንን በፖሊስ መኪና ሲወስዷቸው የዓለም የመገናኛ ብዙሃን ቪዲዮውን አሰራጭተዋል።

አሰልጣኝ ጃማ አደን በስፔይን አበረታች መድሃኒት በመስጠት ተጠርጥረው ታሰሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:08 0:00

በ1980ዎቹና 90ዎቹ የመካከለኛ ርቀት ሯጭ የነበሩት ጀማ አደን በትውልድ ሶማሊያዊ ሲሆኑ የብርታንያ ዜግነትም አላቸው። በዩናይትድ ስቴይትስ የተለያዩ ኮሌጆች የተማሩትና በአሰልጣኝነትም ጭምር ያገለገሉት ጀማ አደን፤ የኢትዮጵያዊቷ የ1500 ሜትር አለም ሻምፒዮና ገንዘቤ ዲባባ አሰልጣኝ ናቸው።

አደን በኢትዮጵያ የኢብራሂም ጀላንና ዳዊት ወልዴ አሰልጣኝ ሲሆኑ። ዜግነታቸው ለውጠው ለተባበረው አረብ ኢምሬት የሚሮጡት ቤተልሄም ደሳለኝና መዲና ሞሃመድ እንዲሁም የባህሬኗ ሚሚ በለጠ አሰልጣኝ ናቸው። የጅቡቲው ሱሌይማን አያልነህም የሚሰለጥነው በጀማ አድን ነው። በተጨማሪም ጀማ የኳታር ቡድን አስልጣኝና አማካሪ ሆነው ሰርተዋል፤ ይሰራሉ።

የስፔይን የፖሊስ ሃይል ቃል አቀባይ ቴራን ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ሁለት ሰዎች መታሰራቸውንና በዛሬውለት አንድ ተጨማሪ ሰው በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጸዋል።

የስፔይን ፖሊስ ከታሳሪዎቹ አንዱ አሰልጣኝ መሆናቸውን ከማስታወቁ ውጭ ስማቸውን ይፋ ከማድረግ ተቆጥቧል። በአድን ክፍል ውስጥ የተከለከለ አበረታች መድሃኒት ተገኝቷል ሲሉ የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ የስፔይን ፖሊስ የሰጠው ማረጋገጫ የለም።

በሳባዴል ከተማ በሚገኝ ሆቴል ውስጥ በርካታ አትሌቶች የሩጫ ልምምድ ለማድረግ ከአለም ዙሪያ ተሰባስበው ነበር። የአለም የጸረ-አበረታች መድሃኒት ድርጅትና የዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሃኪሞች በሆቴሉ ውስጥ የነበሩትን አትሌሎች የደም ናሙና መውሰዳቸውንም የስፔይን ፖሊስ ቃል አቀባይ ገልጸዋል።

“የደም ናሙናው በዓለምአቀፍ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተወሰደ ነው። የዓለምአቀፍ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሃኪሞች ወደ 27 ወይ 28 አትሌቶችን የደም ናሙና ወስደዋል።”

የምርመራው ውጤት እስካሁን አልታወቀም። ሆኖም የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌደሬሽን የጀማ አደንን መታሰር አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ እንዲህ ብሏል።

“የርቀት ሩጫ አሰልጣኝ ጀማ አደን እስራት ከ2005 ዓ.ም ጀመሮ የተካሄደ ምርመራ ውጤት ነው። ከአለም አቀፍ ፖሊስ (ኢንተርፖል)እና የስፔይን ባለስልጣናትና የስፔይን ብሄራዊ የጸረ-አበረታች መድሃኒት ቢሮ ጋር በመተባበር ለዓመታት ያደረግንው ክትትል ነው።”

ዓለምአቀፍ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን በመግለጫው አክሎም ንጹህ አትሌቶችን ለመከታተል በሙሉ አቅሙ እንደሚሰራና እርምጃ እንደሚወስድ፤ በተለይ ጎበዝ አትሌቶች የተከለከሉ መድሃኒቶችን እንዲጠቀሙ የሚያማልሉ አሰልጣኖችና ግለሰቦችን ለማስቆም በትብብር እንደሚሰራ ገልጿል።

የጃማ አደን እስራት፤ በአትሌቶቹ ላይ ክስም ወይንም ወንጀላም አይደለም። የደም ምርመራውና ከጀማ አደን የሚገኘው የፖሊስ ምርመራ ውጤት ግን ወደፊት የሚታወቅ ይሆናል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

የገንዘቤ ዲባባ አሰልጣኝ በስፔይን አበረታች መድሃኒት በመስጠት ተጠርጥረው ታሰሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:47 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG