በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጃክሰን የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሥራቸውን የሚጀመሩበት አጭር ሥነ ሥርዓት ይካሄዳል


ፎቶ ፋይል፦ በዩናይትድ ስቴትስ የጠቅላይ ፍርድ ቤት የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት ዳኛ ሆነው ባላፈው ሚያዝያ የተሾሙት ከታንጂ ብራዎን ጃክሰን
ፎቶ ፋይል፦ በዩናይትድ ስቴትስ የጠቅላይ ፍርድ ቤት የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት ዳኛ ሆነው ባላፈው ሚያዝያ የተሾሙት ከታንጂ ብራዎን ጃክሰን

በዩናይትድ ስቴትስ የጠቅላይ ፍርድ ቤት የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት ዳኛ ሆነው ባላፈው ሚያዝያ የተሾሙት ከታንጂ ብራዎን ጃክሰን በፍርድ ቤቱ አዲሱን የሥራ ዘመን ከሚጀምርበት ሦስት ቀናት በፊት፣ ዛሬ በሚካሄደው አጭር የችሎቱ የወግ ሥነ ሥርዓት ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ይሰየማሉ፡፡

ለአዲሲቷ ዳኛ የክብርና መልካም ምኞት መግለጫው ሥነ ሥርዓት ላይ ፕሬዚዳንት ባይደንና ምክትል ፕሬዚዳንት ከማላ ኻሪስ ከነባለቤቶቻቸው እንደሚገኙ ይጠበቃል፡፡

ከ1965 ዓም ጀምሮ በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ አዲስ የሚሰየሙ ዳኞችን በ1800ዎቹ መጀመሪያ ለ34 ዓመታት የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዋና ዳኛ ሆነው ባገለገሉት ጆን ማርሻል መንበር ላይ እንዲቀመጡ ማድረግ የተለመደ የወግ ሥርዓት መሆኑ ተመልክቷል፡፡

በዚህም የወግ ልማድ መሠረት ለመጀመሪያ ጊዜ በፍርድ ቤቱ የሚታዩት የ52 ዓመቷ ጃክሰንም ዛሬ በመንበሩ ላይ እንደሚሰየሙ የአሶሽየትድ ፕሬስ ዘገባ አመለክቷል፡፡

የባሪያ አሳዳሪ እንደነበሩ በተነገረላቸው ማርሻል ወንበር ላይ መሰየማቸው በፍርድ ቤቱ ታሪክ ለመጀመሪዪቱ ጥቁር ሴት ዳኛ ጃክሰን የተለየ ስሜት ሊያሳድርባቸው እንደሚችልም ዘገባው አመልክቷል፡፡

በፍርድ ቤቱ ታሪክ ከአዲሶቹ ባልደረቦቻቸው ዳኛ ክላነረንስ ቶማስ እና በህይወት ከሌሉት ትሩጉድ ማርሻል ቀጥሎ ጃክሰን ሦስተኛዋ ጥቁር ዳኛ መሆናቸውም ተመልክቷል፡፡

ባላፈው ሚያዝያ ሶስት የሪፐብኪላን አባላትን ጨምሮ የሁሉንም ዴሞክራቶች ድጋፍ በማግኘት 53 ለ47 በሆነ ድምፅ በህግ መወሰኛው ምክር ቤት ሹመታቸው የጸደቀላቸው ጃክሰን በጡረታ የተገለሉትን ስቴፈን ብሬየርን በመተካት በፕሬዚዳንት ባይደን የተመረጡ መሆኑ ይታወሳል፡፡

XS
SM
MD
LG