በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባግቦን ነፃ በመባላቸው ዐቃብያነ ህግ ይግባኝ እንጠይቃለን አሉ


የቀድሞ የአይቮሪኮስት ፕሬዚዳንት ሎሬንት ባግቦን
የቀድሞ የአይቮሪኮስት ፕሬዚዳንት ሎሬንት ባግቦን

የዓለማቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ዳኞች፣ በጦር ወንጀለኛነት የተከሰሱትን የቀድሞ የአይቮሪኮስት ፕሬዚዳንት ሎሬንት ባግቦን ነፃ በማለቱ፣ “ይግባኝ እንጠይቃለን” ሲሉ፣ ዐቃብያነ ህግ አስታወቁ።

የዓለማቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ዳኞች፣ በጦር ወንጀለኛነት የተከሰሱትን የቀድሞ የአይቮሪኮስት ፕሬዚዳንት ሎሬንት ባግቦን ነፃ በማለቱ፣ “ይግባኝ እንጠይቃለን” ሲሉ፣ ዐቃብያነ ህግ አስታወቁ።

የዓለማቀፉ ፍርድ ቤት ዳኞች ትናንት ማክሰኞ ነበር፣ ባግቦ፣ እአአ ከ2010 ምርጫ ጋር ተያይዞ በተቀሰቀሰ አመፅ፣ የጦር ወንጀል ፈፅመዋል ተብሎ ከቀረበባቸው ክሰ ነፃ ያላቸው።

እናም ሦስቱ ዳኞች፣ የ73 ዓመቱን የቀድሞ ፕሬዚዳንት ባግቦን፣ እንዲሁም የርሳቸውን የቅርብ ረዳትና የቀድሞ የወጣቶች ሚኒስትር ቻርልስ ብሌ ጎዴን “ነፃ” በማለት በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ማዘዛቸው አይዘነጋም።

“ይግባኝ እንጠይቃለን” ያሉት ዐቃብያነ ህግ ለዳኞቹ በላኩት ማስታወሻ፣ “ባግቦም ሆኑ ረዳታቸው ቻርልስ ነፃ ስለተባሉ ከሀገር ሊወጡ ስለሚችሉ፣ ከዕይታ እንዳይርቁ ፍርድ ቤቱ ማዛዣ እንዲያወጣባቸው አሳስበዋል።

ባግቦ በአልሳኒ ኦታራ መሸነፋቸውን ባለመቀበላቸው፣ እአአ በ2010 ዓ. ም ማብቂያና በ2011 መጀመሪያ ላይ በነበረው አመፅ፣ ከ3,000 በላይ ሕዝብ መሞቱ ይታወቃል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG