በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢቫንካ ትራምፕ ለኮሚቴው ምስክርነታቸውን ሰጡ


ፎቶ ፋይል፦ የቀደሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የመጀመሪያ ሴት ልጅ፣ ኢቫንካ ትራምፕ
ፎቶ ፋይል፦ የቀደሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የመጀመሪያ ሴት ልጅ፣ ኢቫንካ ትራምፕ

የቀደሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የመጀመሪያ ሴት ልጅ፣ ኢቫንካ ትራምፕና ከፍተኛ ረዳታቸው በትናንትናው እለት የምስክርነት ቃላቸውን ለመስጠት በተወካዮች ምክር ቤት መርማሪ ኮሚቴዎች ፊት ቀርበዋል፡፡

እኤአ ጥር 6 2021 በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ህንጻ ላይ የተፈጸመውን የአመጽ ጥቃት በሚመረምረው የምክር ቤቱ ኮሚቴ ፊት የቀረቡት ኢቫንካ ቃላቸውን የሰጡት በርቀት ሆነው ካሉበት መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ኢቫንካ የቀረቡት ባለቤታቸው ጃሬድ ኩሽነርና ሌላ አንድ ከፍተኛ የዋይት ኃውስ አማካሪ በኮሚቴው ፊት ከቀረቡ አንድ ቀን በኋላ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ህግ አውጭዎቹ ኢቫንካ በአመጹ ወቅት ስለነበራቸው ድርሻ ጠይቀዋቸዋል፡፡

አባታቸው ትራምፕ ምክትል ፕሬዚዳንታቸው ማይክ ፔንስን ምክር ቤቱ በምርጫው የባይደንን አሸናፊነት እንዳያረጋግጥ እንዲያግዱላቸው ስላቀረቡት ጥያቄም ኢቫንካ እንዲያስረዱ መጠየቃቸው ተመልክቷል፡፡

ትራምፕ በወቅቱ አመጸኞችን እንዲያስቆሙ በርካታ ልመናዎች የደረሷቸው ሲሆን፣ ከነዚህ ውስጥ ቢያንስ ሁለቱ ከልጃቸው ኢቫንካ ትራምፕ የቀረቡ መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡

ከአመጹ ጋር በተያያዘ እስካሁን ከ200 ሰዎች በላይ ጥፋተኛ ተብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG