በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢቫንካ ትረምፕ የአይቮሪ ኮስት ቆይታ


ኢቫንካ ትረምፕ
ኢቫንካ ትረምፕ

በአፍሪካ የአራት ቀናት ጉብኝት ያደረጉት የዋይት ሃውስ ከፍተኛ አማካሪ ኢቫንካ ትረምፕ በትናንት የአይቮሪ ኮስት ውሏቸው በሴት ሥራ ፈጣሪዎች ጉባዔ ላይ ተገኝተው ተናግረዋል።

“የምርምርና ጥናቶች ውጤቶች ሁሉ እንደሚያሳዩን የሴቶችን የወሣኝነት አቅም የሚገነቡ ማኅበረሰቦች ይበልጥ ሰላማዊና የበለፀጉ ናቸው” ብለዋል ሚስ ትረምፕ በሴቶች የንግድ ባለቤቶች፣ የማኅበረሰብ አደራጆች፣ ፖለቲከኞችና ተማሪዎች ለተሞላው አዳራሽ።

በማደግ ላይ ያሉ ሃገሮች ሴቶችን አቅም ለመገንባት በሚል አባታቸው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ባለፈው የካቲት ያወጁትን የሃምሣ ሚሊየን ዶላር ዕቅድ ለማስጀመርና ለማበረታታት ወደ ኢትዮጵያና አፍሪካ የተጓዙት ኢቫንካ ትረምፕ ዕቅዱ በመጭዎቹ ስድስት ዓመታት ውስጥ የሃምሣ ሚሊየን ሴቶችን አቅም እንደሚገነባ በአይቮሪ ኮስቱ የሴት ሥራ ፈጣሪዎች የገንዘብ ውጥን ጉባዔ ላይ ተናግረዋል።

የሴቶች ዓለምአቀፍ ልማትና ብልፅግና ተነሣሽነት የሚባለው የፕሬዚዳንት ትረምፕ ዕቅድ ሙሉ በሙሉ የመንግሥት የሆነ ሴቶችን ምጣኔ ኃብታዊ አቅም ለማሳደግ የታሰበ የመጀመሪያው መርኃግብር መሆኑንም ኢቫንካ አመልክተዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG