የኢጣልያ ፍርድ ቤት ነው ሜዲትሬንያን ባሕር ውስጥ ሕወታቸውን ላጡ በመቶዎች ለሚቆጠሩ ፍልሰተኞች ሞት ተጠያቂ ባለው ቱኒዝያዊ የመርከብ አዛዥ ላይ የ18 ዓመት እስራት የበየነው።
ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ የተፈፀመ ከፍተኛው እልቂት የተባለው ይህ አደጋ የደረሰው፣ እ.አ.አ በሚያዝያ ወር 2015 ዓ.ም ወደ አውሮፓ በመሰደድ ላይ የነበሩ ቢያንስ 7መቶ የሚሆኑ ፍልሰተኞች ሜዲትሬንያን ባሕር ውስጥ በመግባታቸው ነው።
ችሎታ ሳይኖረው የመርከብ አዛዥ የነበረው ሙሐመድ አሊ ማሌክ በህገ-ወጥ አጓጓዥነትና በነፍስ ግድያም ተጠያቂ ስለሆነ ነው የ18 ዓመቱ እስራት የተበየነበት።