በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ጣልያን በዓለምቀፍ ሕግ ፍልሰተኞቹን የመቀባል ግዴት አለባት" ኢማኑኤል ማክሮን

ጣልያን መንግሥት ሕይወታቸውን ባተረፈው መርከብ ውስጥ የነበሩትን በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ፍልሰተኞችን አልቀበልም በማለቱ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን መንግሥቱን ከማውገዛቸው ጋር በተያያዘ ኢጣልያ ዛሬ የፈረንሳዩን አምባሳደር ጠርታ አነጋግራለች።

ጣልያን መንግሥት ሕይወታቸውን ባተረፈው መርከብ ውስጥ የነበሩትን በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ፍልሰተኞችን አልቀበልም በማለቱ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን መንግሥቱን ከማውገዛቸው ጋር በተያያዘ ኢጣልያ ዛሬ የፈረንሳዩን አምባሳደር ጠርታ አነጋግራለች።

ጣልያን በዓለምቀፍ ሕግ መሰረት ፍልሰተኞቹን የመቀባል ግዴት አለባት ብለዋል ማክሮን። አብዛኞቹ ፍልሰተኞች ከሰሀራ በመለስ ካሉት የአፍሪካ ሀገሮች የተሰደዱ ናቸው።

የፈረንሳይ መንግሥት ቃል አቀባይ ቤንጃሚን ግሪቬክስ በተናገሩት መሰረት የኢጣልያ መንግሥት በእንዲህ አይነት ሰብዓዊ ህኔታ ላይ ያሳየው ባህሪ ኃላፊናት የጎደለው ነው ሲሉ ለካቢኒያቸው አስገንዝዋል።

አዲሱ የጣልያን የአገር አስተዳደር ሚኒትር ማቲዬ ሳለቪኒ ዛሬ ለህግ መወሰኛ ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር ፈረንሳይ ራስዋ ብዙ ተጨማሪ ፍልሰተኞችን መቀበል አለባት። ማክሮን ከቃላት ወደ ተግባር ማምራት ይኖርባቸዋል የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG