በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፍልሰተኞች የክረምቱ መከራ በጣልያን


ይህ ጥቅስ ፍልሰተኞች ያሰፈሩት ነው
ይህ ጥቅስ ፍልሰተኞች ያሰፈሩት ነው

ወደ ኢጣልያ የሚገቡ ስደተኞችና ፍልሰተኞች ቁጥር እየቀነሰ የመጣ ይምሰል እንጂ ከፈረንሣይ ጋር በምትዋሰነው ውቢቱ ቬንቲሚግሊያ ከተማ ያለው ሁኔታ ግን የሚያሳየው እንደዚያ ዓይነቱን እውነት አይደለም።

ብዙዎቹ ፍልሰተኞች ወደ ፈረንሣይ ለማቋረጥ እየሞከሩና እየጠበቁ ባሉበት በዚህ ጊዜ የአውሮፓው የክረምት ወራት ብርድ እጅግ እየበረታ ሲሆን አንዳንዶቹ በዚያ ጥረታቸው ውስጥ ሕይወታቸውን ከፍለዋል።

የተሻለ ሕይወትን ፍለጋ ነው ፍልሰተኞቹን ገፍቶ አሁን ያሉበት ሁኔታ ላይ ያደረሣቸው። ከዚህ በኋላም ቢሆን ሕይወታቸውን ሊጠይቅ ለሚችል ጉዞ ወደ ፈረንሣይ ከመቀጠላቸው በፊት የተወሰነ ጊዜ ቬንቲሚግሊያ ላይ እያሳለፉ ናቸው።

የክረምቱ ብርታት ግን ያንን የቀጣይ መንገድ ተስፋቸውን ዛሬውኑ አብዝቶ እየተፈታተነው መሆኑን ከዳርፉር ሱዳን የተሰደደው ኢሳ አብደል ሳሌም ለቪኦኤ ተናግሯል።

ቬንቲሚግሊያ ጥንታዊትም ታሪካዊትም፣ ውብም ነችና ጎብኚ አያጣትም። የወንዟን ዳርቻዎች ለመቃኘት ብቅ ለሚል ሰው ታዲያ ከሰሃራ በስተደቡብ ካለው አፍሪካ ፈልሰው የተኮለኮሉ ሰዎችንና አሻራቸውን ማስተዋል የተለመደ ሆኗል።

ከዚያ ወደ ፈረንሣይ መዝለቅ በጣም ከባድ እንደሆነ ነው የሚነገረው።

የፍልሰተኞች የክረምቱ መከራ በጣልያን
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:11 0:00

ከቬንቲሚግሊያ እየተነሱ ወደ ፈረንሣይ የሚሄዱ ባቡሮችን ወሰኑን የሚጠብቁት የፈረንሣይ ፖሊስ መኮንኖች እያበጠሩ ይፈትሿቸውና ያገኙትን ማንንም ፍልሰተኛ ወዲያው ወደመጣበት ይመልሱታል።

ወደአውሮፓ የሚዘልቁ ፍልሰተኞች ጥገኝነት የሚጠይቁ ከሆነ ማመልከቻቸውን መጀመሪያ የረገጡበት ሃገር ላይ እንዲያስገቡ በሕግ ይጠበቅባቸዋል።

ብዙዎቹ ፍልስተኞች ከኢጣልያ ተነስተው ፈረንሣይ ለመግባት ‘የሞት ድልድይ’ ወይም ‘የሞት መተላለፊያ’ ተብለው የሚጠሩትን የአልፕስ ተራሮች ውጣ ውረድ የሚያቋርጥ ከባድ መሥመር በእግራቸው ይያያዙታል፤ ወይም ደግሞ ጥቂት ወጣ ይሉና መኪኖች በሚንቀሳቀሱባቸው ማቋረጫዎች ለመሹለክ ይሞክራሉ።

ባለፉት 15 ወራት ቬንቲሚግሊያ ውስጥ በዚህ አስቸጋሪ ጉዞ ምክንያት 11 ስደተኞች መሞታቸውን ሪፖርቶች ይናገራሉ።

በሌላ በኩል ደግሞ የዚህ አስቸጋሪና ከባድ ጉዞ ሰለባ ከሆኑት መካከል መብቶቻቸውና ደኅንነታቸው እየተጨፈላለቀ ያለ ሕፃናት እንደሚገኙ ኦክስፋም የሚባለው መንግሥታዊ ያልሆነ ግብረ ሰናይ ድርጅት ባልደረባ ኪያራ ሮማንጎ ለቪኦኤ ገልፀዋል።

ለተጨማሪ የተያያዙትን የድምፅና የቪድዮ ፋይሎች ከፍተው ያዳምጡ፤ ይመልከቱ።

የፍልሰተኞች የክረምቱ መከራ በጣልያን
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:49 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG