በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጣሊያን ልትመርጥ ነው


ጆርጂያ መሎኒ
ጆርጂያ መሎኒ

አውሮፓ በዩክሬን እየተካሄደ ባለው ጦርነት ሳቢያ ችግር ላይ በወደቀችበት በዚህ ወቅት፣ ጣሊያናውያን በመጪው እሁድ ወደ ድምጽ መስጫ ያመራሉ።

ወሳኝ በተባለው በዚህ ምርጫ፣ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ለመጀመሪያ ግዜ፣ ቀኝ አክራሪ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ወንበር ሊወስድ ይችላል እየተባለ ነው።

በዩክሬኑ ጦርነት ምክንያት ያሻቀበው የነዳጅና የዳቦ ዋጋ፣ በርካታ ጣልያናዊ ቤተሰቦችንና ንግዳቸውን ክፉኛ ጎድቷል ሲል አሶሲዬትድ ፕረስ ዘግቧል።

ጆርጂያ መሎኒ እና የኒዎ-ፋሺስት መሰረት ያለውና ሃይማኖተኛው፣ “የጣሊያን ወንድሞች” የተሰኘው ፓርቲያቸው በጣሊያን ምርጫ ከፊት እየመራ ያለ ነው ተብሏል።

ምርጫው 27 ሀገሮች አባል በሁኑባት የአውሮፓ ሕብረት የቀኝ አክራሪነት ተቀባይነት ያገኝ እንደሁ መሞከሪያ ነው ተብሏል።

የመሎኒ ተባባሪና የቀኝ ክንፉ “ሊግ ፓርቲ” መሪ ያሆኑት ማቲዮ ሳልቪኒ በጣሊያን የሚፈጸኑ ወንጀሎችን ሁሉ በፍልሰተኛው ያላክካሉ። ሳልቪኒ በሃንጋሪና በፖላንድ የቀኝ አክራሪ መንግሥት እንዲኖር ጠንካራ ርዕዮተ ዓለማዊ ድጋፍ ሲያደርጉ ቆይተዋል።

“በኢኮኖሚ ጫናና በነዳጅ ችግር ምክንያት ‘አውሮፓ ትሰባበራለች’ ብለው ፑቲን እየጠበቁ ነው ሲሉ መሰረቱን ሮም ያደረገ የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተቋም ሃላፊ የሆኑት ናታሊ ቶቺ ለአሶስዬትድ ፕረስ ተናግረዋል።

ሳልቪኒ ፑቲንን የሚደግፍ ካሪንቴራ ከዚህ በፊት ለብስው ታይተዋል። “ምዕራቡ ዓለም በሩሲያ ላይ የጣለው ማዕቀብ ብልህነት ይጎድለዋል፣ ጣልያንንም በጣም ይጎዳል” ባይ ናቸው።

በሲሲሊ “የጣሊያን ወንድሞች” ፓርቲ ተወዳዳሪ ሂትለርን በማወደሳቸው ከምርጫው ታግደዋል። የመሎኒ ፓርቲ አጋር መስራች የሆኑ ግለሰብ ወንድም ደግሞ በአንድ የቀብር ሥነ ስርዓት ላይ የፋሺስቶችን ሠላምታ ሰጥቷል በሚል ሲወነጀል፣ እርሱ ግን ማድረጉን ክዷል።

በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ፍልሰተኞች በአዘዋዋሪዎች ጀልባ ወደ ጣሊያን መምጣታቸውንና፣ የቀኝ አክራሪዎች “ማቆሚያ ለሌለው” የሚሉትን ፍልሰት በመቃወም የምርጫ ዘመቻ ሲያደርጉ ከርመዋል። መሎኒም ሆነ ሳልቪኒ የጣሊያንን ክርስቲያናዊ ባህሪ የማይቀበሉ በሚሏቸው መጤዎች ላይ ምሬታችውን ያሰማሉ።

ከመሎኒና ሳልቪኒ በተቃራኒ የቆሙት የግራ ዘመሙ “ዲሞክራቲክ ፓርቲ” መሪና የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤንሪኮ ለታ ናቸው። እርሳቸው በህጋዊ መንገድ ለመጡ ስደተኞች ለልጆቻቸው ዜግነት እንዲያገኙ ለማመቻቸት ይፈልጋሉ።

XS
SM
MD
LG