በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጣሊያን 12 የሕገ ወጥ አስተላላፊ ቡድን አባላትን አሰረች


የጣሊያን ፖሊስ
የጣሊያን ፖሊስ

የጣሊያን ፖሊስ በቱኒዝያ የባህር ዳርቻ እና በሲሲሊ ወደቦች መካከል በከፍተኛ ፍጥነት በሚቀዝፉ ጀልባዎች ሥደተኞች በሕገ ወጥ መንገድ በማስተላለፍ ወንጀል የተጠረጠሩ 12 ግለሰቦች አሰረ።

ለሌሎች ስድስት ተጠርጣሪ የሕገ ወጥ አስተላላፊ ቡድኑ አባላት ደግሞ የእስር ማዘዣ አወጣ። ግለሰቦቹ የጣሊያን እና የቱኒዚያ ተወላጆች መሆናቸውም ተመልክቷል።

ተጠርጣሪዎቹ አንድ ሰው በሕገ ወጥ መንገድ ለማስተላለፍ ከ3,000 እስከ 5,000 ዩሮ (ከ3,100 እስከ 5,200 ዶላር) በጥሬ ገንዘብ እንዲከፍሉ በመጠየቅ እና በአንድ ጊዜ ከ10 እስከ 30 ተሳፋሪዎችን በጀልባዎቹ አጭቀው በመጫን፣ ለእያንዳንዱ አራት ሰዓት የሚወስድ ጉዞ ከ30,000-70,000 ዩሮ በመሰብሰብ ነው የተወነጀሉት።

ፖሊስ በሰጠው መግለጫ እአአ የካቲት 2019 በሲሲሊ የገላ ወደብ አቅራቢያ የሚኖር አንድ ዓሣ አስጋሪ 10 ሜትር ርዝማኔ ያላት አንዲት ባለ ሁለት፣ 200 የፈረስ ጉልበት ጀልባ ማየቱን መናገሩን ተከትሎ ምርመራ መጀመሩን አስታውቋል።

መርማሪዎች ጀልባዋ ከሲሲሊዋ ካታኒያ የተሰረቀች መሆኗን ደርሰውበታል።

XS
SM
MD
LG