በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካውያን ፍልሰት እና የጣሊያንና የፈረንሳይ የዲፕሎማሲ ግጭት


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

“ዛሬም አፍሪካን ጥለው የሚሰደዱ ሰዎች ካሉ፤ በበርካታ የአፍሪካ አገሮች ሳቢያ ነው። የመጀመሪያዋም አፍሪካን ቅኝ መግዛቷን ያላቆመችው ፈረንሳይ ናት።” የጣሊያኑ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ሉዊ ጂ ዲሜዮ። “የሕብረቱን ፋይዳ በጥርጣሬ የሚመለከቱና ግለኝነት የሚያቀቅኑ ብሔርተኞች የአውሮፓ ሕዝብ ከሚሰማው ስጋት ለማትረፍ ይጥራሉ። “ለሥጋትህም መልሱ ብሔርተኝነት ነው ይሉታል።” የፈረንሳዩ ጠቅላይ ሚንስትር ኢማኑኤል ማክሮን።

የጣሊያኑ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር “የአፍሪቃ አገሮችን እንዲቆረቁዙ አድርጋለች” ሲሉ ፈረንሳይን የወነጀሉበት አስተያየት፤ በሁለቱ አውሮፓውያን ተጎራባቾች መካከል አንዳች ስንጥቅ ፈጥሯል።

የእሰጥ-አገባው መንሴም በቅርቡ በመቶዎች የሚቆጠሩ አፍሪቃውያን ስደተኞች ከሜዲትራንያኑ የሊቢያ ባሕር ሰጥመው ላለቁበት ድንገት ምክኒያት የሆነው አፍሪቃውያን ስደተኞች ወደ አውሮፓ የሚያደርጉት አደገኛ የፍልሰት ጉዞ ነው።

ንትርኩ የፊታችን ግንቦት ከሚካሄደው የአውሮፓውያኑ ምርጫ አስቀድሞ በአሕጉሪቱ አገሮች መካከል ይቀሰቀሳል ተብሎ የሚፈራ ብርቱ መከፋፈል ማሳያ ነውም ተብሏል።

ቀድሞውኑ ክፉኛ መቀዛቀዝ ይታይበት የነበረው የፓሪስና የሮም ግንኙነት፤ አሁን ከለየለት የዲፕሎማሲ በረዶ ውስጥ ተዘፍቋል። ባለፈው እሁድ የጣሊያኑ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ሉዊ ጂ ዲሜዮ የሰጡትን አስተያየት እንዲያብራሩ ፈረንሳይ የጣሊያኑን አምባሳደር ጠርታ አነጋግራለች።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የአፍሪካውያን ፍልሰት እና የጣሊያንና የፈረንሳይ የዲፕሎማሲ ግጭት
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:08 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG