በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጠቅላይ ሚኒስትር ሜሎኒ የፍልስተኞቹ ፖሊሲ አልሠራም አሉ


የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ
የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ

የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ መንግሥታቸው ፍልስተኞችን በመቆጣጠር ረገድ ደካማ አፈጻጸም ማሳየቱንና ፖሊሲውም አለመሥራቱን ተናገሩ፡፡

ሜሎኒ በተለያዩ አብይ ጉዳዮች ላይ ትናንት ሐሙስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በመንግሥታቸው የፍልስተኞች ፖሊስ ውስጥ ያሉትን ተግዳሮቶችና ድክመቶች አጉልተው በማውጣት የመፍትሄ ሀሳቦች ናቸው ያሏቸውንም አብራርተዋል፡፡

በርዳታ ብቻ ከመተማመን የፍልስተኞች ምንጭ ለመግታት ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ለተጠናከረ አጋርነት ኢንቨስት ማድረግ እንደሚያስፈልግ ጠቅላይ ሚኒስትሯ ለአውሮፓ አጋሮቻቸው ተናግረዋል፡፡

ሜሎኒ በቅርቡ የአውሮፓ ህብረት የፍልሰት እና የጥገኝነት ስምምነት ማድረጉ ለጣሊያን እና ለሌሎች ጥገኝነት ተቀባይ ሀገራት መጠነኛ መሻሻሎችን ቢያመጣም፣ እየጨመረ ለመጣው የፍልስተኞች ችግር ግን ሁሉን አቀፍ መፍትሄ ይጎድለዋል ብለዋል።

የህጋዊ ስደት መንገዶችን አስፈላጊነት ለማሳየት ወደ አውሮፓ ለመሰደድ ብቁ የሆኑ ግለሰቦችን ሁኔታ የሚገመግሙ ቦታዎች እዚያው አፍሪካ ውስጥ እንዲመሰረቱም ሜሎኒ ሀሳብ አቅርበዋል፡፡

እኤአ በ2023 ወደ ጣሊያን የገቡ ፍልስተኞች ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የሃምሳ በመቶ (50%) ጭማሪ ማሳየቱን መረጃዎች የጠቀሰው አሶሴይትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

ፍልሰትን ለማስቆም ቃል ገብተው ለተመረጡት የጣልያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ትልቅ ፈተና ነው ተብሏል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG