በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአል-አቅሳ ውጥረት እንደከረረ ነው


እሥራኤል ለአይሁድም ለሙስሊሞችም የጋራ በሆነው ቅዱስና የአምልኮ ሥፍራ ላይ የብረት መለያ መፈተሻ መሣሪያዎችን የማቆም እምርጃዋን ብትቀይርም በአካባቢው ያለው ውጥረት አሁንም እንደበረታ መሆኑ ተዘግቧል።

እሥራኤል ለአይሁድም ለሙስሊሞችም የጋራ በሆነው ቅዱስና የአምልኮ ሥፍራ ላይ የብረት መለያ መፈተሻ መሣሪያዎችን የማቆም እምርጃዋን ብትቀይርም በአካባቢው ያለው ውጥረት አሁንም እንደበረታ መሆኑ ተዘግቧል።

በፍልስጥዔማዊያኑ ዘንድ የመረረ ተቃውሞ ያስነሱትን አይሁድ የፅዮን ኮረብታ በሚሉትና በአሮጌዪቱ ኢየሩሣሌም በሚገኘው ለሙስሊሞችም ቅዱስ የአምልኮ ሥፍራ በሆነው አል-አቅሳ መስጅድ ላይ እሥራኤል የተከለቻቸውን የፍተሻ መሣሪያዎች ነቃቅላለች።

የፍተሻ መሣሪያዎቹ የተተከሉት ጠብመንጃ አንጋች አረቦች ከሁለት ሣምንታት በፊት ወደ ግቢው ዘልቀው ሁለት እሥራኤላዊያን ፖሊሶችን ከገደሉ በኋላ ነበር።

ፍልስጥዔማዊያኑ የተቆጡት እሥራኤል የእምነት ነፃነትን ረግጣለች፣ በእሥልምና እምነት ሦስተኛው ቅዱስ ሥፍራ የሆነውን አካባቢሙ በኃይል ለመቆጣጠር እየሞከረች ነው በሚል ሃሣብ ነው።

ፍልስጥዔማዊያኑ ሙስሊሞች በፍተሻ መሣሪያዎቹ ውስጥ አናልፍም ብለው ወደ መስጂዱ በሚያስገቡ መንገዶች ላይ ዘርግተው መፀለይና መስገድ ጀመሩና ውጥረትና ግጭቶች ተቀጣጠሉ።

ጣልቃ ገብተው የመስጂዱ የበላይ ጠባቂ በሆነችው በዮርዳኖስና በእሥራኤል መካከል ማሸማገል የጀመሩት ቴል አቪቭ የሚገኙት የአሜሪካ አምባሣደር ዴቪድ ፍሪድማን “አንዳንድ ጊዜ ነገሮችን ቀድሞ መገኘት አስፈላጊ ነው፤ ያንን ያደረን ይመስለኛል። ብዙ ወሬ ሳናበዛና ከመጋረጃ በስተጀርባ ካደረግነው ብርቱ ሥራ ሁኔታውን ፈጥነን አርግበናል” ብለዋል።

ይሁን እንጂ አጠቃላዩ ሁኔታ ጨርሶ አልረገበም። የፍተሻ መሣሪያዎቹ ቢነሱም ከፍተኛ ጥራት ባላቸው ካሜራዎች መተካታቸው ሙስሊም ባለሥልጣናቱን አላስደሰተም። በመሆኑም ፍልስጥዔማዊያኑ ወደ መስጂዱ እንዳይገቡ አሳስበዋል።

“ሁሉም ነገር ውጥረቱ ከመቀስቀሱ በፊት ወደነበረበት ሁኔታ እንዲመለስ” ፍልስጥዔማዊው ባለሥልጣን ናቢል ሻጥ ጠይቀዋል። “ካሜራዎችም ሆኑ ሌላ ማንኛውም ዓይነት የደኅንነት እርምጃ ሙስሊሞቹን የሚያዋርድና ጨርሶ ተቀባይነት የሌለው ነው” ብለዋል ናቢል ሻጥ።

ፍልስጥዔማዊያኑ በአካባቢው ፀጥታ እንዲመለስ አይፈልጉም ሲሉ የሚወነጅሉት የእሥራዔል ካቢኔ ሚኒስትር ዩቫል ስቴይኒትዝ “እሥራኤል እሺ ብላ እጅ ብትሰጥም ፍልስጥዔማዊያኑ ግን በሙስሊሞቹና በአይሁድ መካከል የሐይማኖት ጦርነት ለማጫር እየጣሩ ናቸው” ሲሉ ከስሰዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የአል-አቅሳ ውጥረት እንደከረረ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:56 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG