ዋሺንግተን ዲሲ —
የጋዛ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በሰጡት መግለጫ፣ የእሥራኤል ታንክ ከሃነ ከተማ አቅራቢያ ባካሄደው ጥቃት አንድ ፍልስጤማዊ አርሶ አደር ሲሞት ሌላ አንድ መቁሰሉን አስታወቁ።
የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት የዐይን ምስክሮችን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ አርሶ አደሩ የተገደለው እርሻ ማሳው ላይ እንዳለ ነው።
አንድ የእሥራኤል ጦር ቃል አቀባይ እንዳመለከተው፣ ሁለት ተጠርጣሪዎች ደቡባዊ ጋዛ ሰርጥ ወደሚገኘው የደኅንነት ጥበቃ አጥር ቀርበው የሚያስጠረጥር እንቅስቃሴ ሲያደርጉ በመታየታቸው፣ የእሥራኤል ታንክ በአጸፋው ተኩሶባቸዋል።
ሟቹ፣ ኡመር ሳሞረ የተባለ የሃያ ሰባት ዓመት ሰው መሆኑም ተገልጧል።
ዛሬ ባጋጠመ ሌላ አደጋ ደግሞ ሃያ ሰዎች መቁሰላቸውን እየሩሳሌ ፖስት የተባለው ጋዜጣ ዘግቧል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ