በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእስራኤል ጠ/ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ወደሳውዲ አረቢያ መጓዝ


ፎቶ ፋይል፦ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ
ፎቶ ፋይል፦ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ትናንት እሁድ በሚስጥር ወደሳውዲ አረብያ ተጉዘው እንደነበር የሄዱትም ከሳውዲ ልዑል አልጋ ወራሽ መሃመድ ቢን ሳልማን እና ከዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፓምፔዎ ጋር ለመነጋገር እንደነበር ዛሬ እስራኤል መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ።

ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ከተጓዙት መካከል የእስራኤል የብሄራዊ ጸጥታ ድርጅት የሞሳድ ሃላፊ ዮሲ ኮኸን እንደሚገኙባቸው ነው ዘገባዎቹ የጠቀሱት።

ዘገባዎቹ የበረራዎች ክትትል መረጃዎችን ዋቢ አድርገው ሲዘግቡ ትናንት እንዲት የግል ጄት ከቴል አቪቭ ተንስታ ሳውዲ አረቢያ ኒዮም ከተማ ካረፈች በኋላ ጥቂት ሰዓታት ቆይታ ተመልሳለች ብለዋል።

ዘገባዎቹን በተመለከተ ከጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ጽህፈት ቤት የተሰጠ አስተያየት የለም።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም ሚኒስትር ፖምፒዎ ኒዎም ከተማ ላይ ከሳውዲው አልጋ ወራሽ መሃመድ ቢን ሳልማን ጋር መነጋገራቸውን አስመልክቶ ትናንት ዕሁድ ባወጣው መግለጫ ላይ የእስራዔል ጠቅላይ ሚንስትር ኔታንያሁን አላነሳም።

የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ተቀዳሚ ምክትል ቃል አቀባይ ኬል ብራውን "የሳውዲ አልጋ ወራሽ እና ሚኒስትር ፖምፔዎ" ኢራን በክልሉ የምታሳየውን የጉልበተኝነት ባህሪ ለመገዳደር የሰላጤ ሃገሮች በአንድነት መቆም እንዳለባቸው ለየመኑ ግጭት የፖለቲካ መፍትሄ ማግኘት አስፈላጊ መሆኑን በተመለከተ ተወያይተዋል።

XS
SM
MD
LG