በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በእሥራኤል ወታደሮች ላይ ጥቃት በማድረስ ክስ የተመሰረተባት ፍልስጤማዊ ችሎት


Ahed Tamimi
Ahed Tamimi

በሁለት የእሥራኤል ወታደሮች ላይ ጥቃት በማድረሷ ክስ የተመሰረተባት ወጣት ፍልስጤማዊ ችሎት፣ ዛሬ በአንድ የእሥራኤል ወታደራዊ ፍርድ ቤት ተከፈተ።

በሁለት የእሥራኤል ወታደሮች ላይ ጥቃት በማድረሷ ክስ የተመሰረተባት ወጣት ፍልስጤማዊ ችሎት፣ ዛሬ በአንድ የእሥራኤል ወታደራዊ ፍርድ ቤት ተከፈተ።

ይህ ዓለማቀፍ ትኩረትን የሳበው የክስ ሂደት፣ በዝግ ችሎት እንዲታይ ዳኛው መወሰናቸው ታውቋል።

ወህኒ ቤት ሆና 17ኛ ዓመቷን የያዘችው አሄደ ታሚሚ በጋዜጠኞችና በውጪ ሀገር ዲፕሎማቶች ወደተሞላው የችሎቱ አዳራሽ ስትገባ፣ ሙሉ በራስ የመተማመን ስሜት ይነበብባት እንደነበር ተገልጧል።

ወዲያው፣ እዚያ ለተገኙ ዘመዶቿ አጭር ሰላምታ እንዳቀረበች፣ ዳኛው፣ ከእርሷና ከዘመዶቿ በቀር ሁሉም ችሎቱን ለቆ እንዲወጣ ትዛዝ አስተላልፈዋል።

ታሚሚ፣ ባለፈው ታህሣሥ ወር ነው፣ ሁለት እሥራኤላውያን ወታደሮች ላይ፣ ዌስት ባንክ በሚገኘው የመኖሪያ ስፍራዋ ጥቃት ላታደረስ ስትሞክር በቪዲዮ ከተነሳች በኋላ ወህኒ የወረደችው።

በቪዲዮ መሠረት፣ ታሚሚ አንዱን ወታደር እግሩ ላይ ሌላውን ደግሞ በጥፊ ስትመታው ይታያል።

ጥፋተኛ ሆና ከተገኘች፣ ለዓመታት ያህል በእስር ልትቆይ እንደምትችል ነው የተነገረው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG