በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እሥራኤል በኢራን ወታደራዊ ዒላማዎች የአየር ጥቃት ማካሄዷን አመነች


እሥራኤል፣ ሦርያ ውስጥ በሚገኙ የኢራን ወታደራዊ ዒላማዎች ላይ የአየር ጥቃት ማካሄዷን ዛሬ በሰጠችው ቃል አመነች።

እሥራኤል፣ ሦርያ ውስጥ በሚገኙ የኢራን ወታደራዊ ዒላማዎች ላይ የአየር ጥቃት ማካሄዷን ዛሬ በሰጠችው ቃል አመነች።

የአየር ጥቃቱ የተካሄደው፣ የኢራን ኃይሎች የጎላን ተራራን ዒላማ ያደረገ የመሬት ለመሬት ሮኬት ከሦርያ በመላካቸው ለዚያ የተወሰደ አፀፋ መሆኑን የእሥራኤል ጦር አስታውቋል።

እሥራኤል እንደገለፀችው የአየር ጥቃቷ ዒላማ፣ ደማስቆ የሚገኘው የአውሮፕላን ጣቢያ እንዲሁም ኢራን የሚገኘው የማሰልጠኛ ጣቢያና የጥይት መጋዘን ሆኖ በመጨረሻም የሦርያ የሚሳይል መከላከያ ነበር።

ብሪታንያ የሚገኘውና ጦርነቱን የሚቆጣጠረው የሦርያ ሰብዓዊ መብት ታዛቢ ቡድን፣ የእሥራኤል የአይር ጥቃት 11 አፍቃሪ ሦርያ ተዋጊዎችን እንደገደለ አስታውቋል።

የእሥራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔተናሁ በተናገሩት ቃል፣ እሥራኤል ሊያጠቋት የሚፈልጉትን ማናቸውንም ቢሆን አትምርም ብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG