እስራኤላውያን እና ፍልስጤማውያን ዶናልድ ትራምፕ በዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አሸንፈው የመመረጣቸውን ዜና በደስታ መቀበላቸውን እየገለጡ ነው። ከሁለቱ ወገኖች በኩል ትላንት ረቡዕ በተሰሙት አስተያየቶች፤ እስራኤላውያን ከሃማስ፣ ሄዝቦላ እና ኢራን ጋር እያካሄዱ ባሉት ጦርነት ይረዱናል የሚል ተስፋ ማድረጋቸውን ሲገልጡ፤ ፍልስጤማውያን በበኩላቸው ነጻ የፍልስጤም ግዛት በሚመሰረትበት ሁኔታ ላይ አንዳንድ አዳዲስ ሃሳቦችን ያመጡ ይሆናል የሚል ተስፋ አሳድረዋል።
ሊንዳ ግራድስቲን ከኢየሩሳሌም ያጠናቀረችውን ዘገባ ዝርዝር ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም