በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእስራኤል ወታደሮች ቢላዋ ይዞብን መጣ ያሉትን ፍልስጤማዊ ገደሉ


የእስራኤል ወታደሮች በምዕራብ ጋዛ ዳርቻ ድርጊቱ ተፈጽሞበታል በተባለው የጊቲ አቪሻር አቅራቢያ እአአ 31/2021
የእስራኤል ወታደሮች በምዕራብ ጋዛ ዳርቻ ድርጊቱ ተፈጽሞበታል በተባለው የጊቲ አቪሻር አቅራቢያ እአአ 31/2021

የእስራኤል ወታደሮች ዛሬ ዓርብ በኃይል በተያዘው የምዕራብ ጋዛ ዳርቻ አካባቢ በሚገኝ የአውቶብስ ማቆሚያ ቢላ ይዞ ወደነሱ ሲሮጥ የነበረውን አንድ ፍልስጤማዊ መግደላቸውን የእስራል ጦር አስታወቀ፡፡

ፍልስጤማዊው እስራኤላውያኑ አይሁዶች ወደ ሰፈሩበት አቅራቢያ በመኪና በመምጣት ከመኪናው ውስጥ ቢላዋ ይዞ መውጣቱን በተደረገው የመጀመሪያ ምርመራ መጠቀሱን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

ከመኪናውም ከወጣ በኋላ አውቶብስ ጣቢያው አጠገብ ወደነበሩ ሰላማዊ ሰዎችና የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት አባላት ቆመውበት ወደነበረበት ቦታ ሲያመራ እንደነበርም ተጠቅሷል፡፡

በዩናይትድ ስቴትስ ድጋፍ በፍልስጤምና እስራኤል መካከል ይደረግ የነበረው ድርድር እኤአ በ2014 ከተቋረጠ በኋላ፣ በምዕራብ ጋዛ ዳርቻ አካባቢ ያለው ውጥረት እየተባባሰ መምጣቱ ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG