በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል ደማስቆ ላይ የአየር ጥቃት አደረሰች፦ሶሪያ


 የአየር ጥቃቱ ኢላማ የተደረገበት ህንፃ ከፋር ሶሴህ ደማስቆ፤ ሶሪያ እአአ የካቲት 21/2024
የአየር ጥቃቱ ኢላማ የተደረገበት ህንፃ ከፋር ሶሴህ ደማስቆ፤ ሶሪያ እአአ የካቲት 21/2024

እስራኤል በዋና ከተማዬ ደማስቆ የሚገኝ አንድ የመኖሪያ ቤት ህንፃ ላይ የአየር ጥቃት ፈፅማለች ስትል ሶሪያ አስታወቀች።

የሶሪያ መንግሥት መገናኛ ብዙሀን ዛሬ ረቡዕ ባወጡት ዘገባ “ጥቃቱ የተፈፀመው “ከፋር ሶሴህ” በተባለው የፀጥታ እና ወታደራዊ ተቋማት ዋና ፅህፈት ቤቶች የሚገኙበት አካባቢ ነው” ብለዋል።

ጥቃቱ የተፈፀመው “ከፋር ሶሴህ” በተባለው የፀጥታ እና ወታደራዊ ተቋማት ዋና ፅህፈት ቤቶች የሚገኙበት አካባቢ ነው”

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ሶሪያ ላይ በርካታ የአየር ድብደባዎችን ሲያካሂድ የነበረው የእስራኤል ጦር ስለደረሰው ጥቃት ምንም ዐይነት መግለጫ አልሰጠም።

ጥቃቶች አደረሰች መባሏን ብዙ ጊዜ የማትቀበለው እስራኤል ሶሪያ ውስጥ የምትወስደው ርምጃ ግን በኢራን የሚደገፉ ኃይሎች ላይ ያነጣጠረ መሆኑን ተናግራለች።

ባለፈው ዓመት የካቲት ወር ውስጥም ተመሳሳይ የአየር ድብደባ በዚሁ ዛሬ ጥቃት በተፈፀመበት አካባቢ የተካሄደ ሲሆን በርካታ የኢራን ወታደራዊ ባለሙያዎችን ገድሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG