በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እየሩሳሌም የሚገኝ የባቡር ጣቢያ በፕሬዚዳንት ትረምፕ ስም እንዲሰየም ተጠየቀ

እየሩሳሌም የሚገኘው የተቀደሰው ምዕራባዊው ግንብ አቅራቢያ የሚገነባው የባቡር ጣቢያ በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ስም እንዲሰየም የእስራኤል የትራንስፖርት ሚኒስትር ሃሳብ አቀረቡ።

እየሩሳሌም የሚገኘው የተቀደሰው ምዕራባዊው ግንብ አቅራቢያ የሚገነባው የባቡር ጣቢያ በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ስም እንዲሰየም የእስራኤል የትራንስፖርት ሚኒስትር ሃሳብ አቀረቡ።

ፕሬዚደንት ትረምፕ እየሩሳሌም የእሥራኤል ዋና ከተማ ነች ብለው ዕውቅና መስጥታቸውን ተከትሎ ሚኒስትሩ ዪስራኤል ካትዝ ይህን ሃሳብ ያቀረቡት በቅርቡ በተካሄደ የሀገራቸው የባባሩ መሥመር ዋና ሥራ አስኪያጆች ስብሰባ ላይ ሲሆን በቅርቡ የሚከፈተው የፈጣን ባቡር መሥመር ወደምዕራባዊው ግንብ እንዲዘልቅና እዚያው ጋ አዲስ የባቡር ጣቢያ እንዲሰራ ይጠይቃል።

ፕሬዚደንት ትረምፕ እየሩሳሌምን በእስራኤል ዋና ከተማነት በማወቅ በጀግንነት ስለወሰዱት ታሪካዊ ውሳኔ፣ የባቡር ጣቢያው በስማቸው ይሰየም ሲሉ ነው ሚኒስትሩ ሃሳብ ያቀረቡት ።

ሃሳቡ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ተቃውሞ እንደሚገጥመው ተገምቷል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG