ሃማስ ጋዛ የህፃናት ሆስፒታል ሥር የጦር መሣሪያ ማከማቸቱን ያሳያሉ ያላቸውን ቪዲዮና ፎቶግራፎችን የእሥራኤል ጦር ትላንት ሰኞ፣ አውጥቷል።
‘የእጅ ቦምቦችን፣ በፈንጂ የታጨቁ የአጥፍቶ ጠፊ ሰደርያዎችን፣ የሃማስ ተዋጊዎች እንደ ወታደራዊ ዕዝ ይጠቀሙበት ነበር ባለው ራንቲሲ የሕፃናት ካንሰር ሕክምና ሆስፒታል ሥር አከማችቷል ያሏቸውን የጦር መሣሪያዎች ማግኘታቸውን የሠራዊቱ ቃል አቀባይ ሪር አድሚራል ዳንኤል ሃጋሪ ተናግረዋል።
አዛዡ ያቀረቡት ቪድዮ አነስኛ ማዕድ ቤትን ጨምሮ አንዲት የመኖሪያ ቤት የመሰለች ክፍል ውስጥና በአቅራቢያው ወደሚገኝ የሃማስ የባህር ላይ ውጊያ አዛዥ መኖሪያ ቤት የሚወስድ መተላለፊያን ያሳያል።
ቪዲዮው የተቀረፀበትን ሥፍራና ወቅት በራሱ ማረጋገጥ አለመቻሉን ሮይተርስ በዘገባው ላይ ጠቁሟል።
ሃማስና የጋዛው ሆስፒታል ባለሥልጣናት በበኩላቸው የጤና ተቋማት ለዚህ መሰሉ ወታደራዊ ዓላማ ውለዋል የሚለውን ውንጀላ አስተባብለዋል።
የእስራኤል ጦር ይፋ ያደረገውን መረጃ አስመልክቶ ግን ከሃማስ የተሰጠ ምላሽ እስካሁን የለም።
መድረክ / ፎረም