በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእስራኤል ሀኪሞች በቴል አቪቭ አቅራቢያ ሦስት ሰዎች በስለት ተወግተው መገደላቸውን አስታወቁ


የእስራኤል ኃይሎች በእስራኤል ኢላድ ከተማ በስለት ጥቃት የደረሰበትን አካባቢ ሲጠባበቁ እአአ ግንቦት 5/2022
የእስራኤል ኃይሎች በእስራኤል ኢላድ ከተማ በስለት ጥቃት የደረሰበትን አካባቢ ሲጠባበቁ እአአ ግንቦት 5/2022

እስራኤል ውስጥ በቴል አቪቭ አቅራቢያ በምትገኘው ኢላድ ከተማ ትናንት ሀሙስ በፍስልጤማውያን ተፈጽሟል በተባለ ጥቃት ቢያንስ ሦስት ሰዎች በስለት ተወግተው መገደላቸውን የእስራኤል ሀኪሞች አስታወቁ፡፡

የቴሌ አቪቭ እስራኤል ፖሊሶች ጥቃቱን ያደረሱት ሰዎች በመኪና ማምለጣቸውን አስታውቀዋል፡፡ አደጋው የተፈጸመው እስራኤላውያውን የነጻነት ቀናቸውን በተለያዩ የጎዳና ዝግጅቶችና የአየር ላይ ትርኢቶች በሚያከብሩበት ወቅት መሆኑ ተነግሯል፡፡

ቀደም ሲል በዚሁ እለት፣ ኢየሩሳሌም ውስጥ ለእስራኤላና ፍልስጤማውያን መለኮታዊ በሆኑ የሀይማኖት ተቋማት አቅራቢያ፣ በፍስጤማውያን አዲስ አመጽ ተቀስቅሶ እንደነበር ተነግሯል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በፍልስጤምና እስራኤል መካከል ያለው አለመግባባት እያየለ መምጣቱም ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG