በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፍሪካውያን ፍልሰተኞች በእስራኤል

ፎቶ ፉይል:- አፍሪካውያን ፍልሰተኞች በእስራኤል ቴላ ቪቭ
ፎቶ ፉይል:- አፍሪካውያን ፍልሰተኞች በእስራኤል ቴላ ቪቭ

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ አፍሪካውያን ፍልሰተኞችን በምዕራብ ሀገሮች ለማስፈር ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር አድርገውት የነበረውን ሥምምነት እየሰረዙ መሆናቸውን ዛሬ አስታወቁ።

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ አፍሪካውያን ፍልሰተኞችን በምዕራብ ሀገሮች ለማስፈር ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር አድርገውት የነበረውን ሥምምነት እየሰረዙ መሆናቸውን ዛሬ አስታወቁ።

ኔታንያሁ ስደተኞቹን በምዕራብ ሀገሮች ለማስፈር ሥምምነት ማድረጋቸውን ያስታወቁት ትላንት ሰኞ ነበር። ከሰአታት በኋላ ግን ለምሬቶች ጆሮአቸውን ከሰጡና ሁኔታዎችን ከገመገሙ በኋል ሥምምነቱን እየሰረዙ መሆናቸውን አስታወቁ።

መጀመርያ ላይ በተደረገው ስምምነት መሰረት 16,250 የሚሆኑ ፍልሰተኞች ወደ ካናዳ፣ ኢጣልያና ጀርመን ሊላኩ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል። ኋላ ግን ጀርመን አሪካውያን መጤዎችን ስለማስፈሩ እቅድ እማውቀው ነገር የለም ማለትዋ ተግልጿል።

እስራኤል ውስጥ በ 35,000 የሚገመቱ አፍሪካውያን ሰደተኞች አሉ። አብዛኞቹ በአለም ደረጃ አስከፊ የሰብአዊ መብት አያያዝ አላቸው ከሚባሉት ሀገሮች መካከል ከምትፈረጀው ኤርትራ ወይም በጦርነት ከላሸቀችው ሱዳን የተሰደዱ ናቸው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG