በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል ዓለማቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያዎቿን ልትዘጋ ነው


ፎቶ ፋይል፦ ቤን ጉሪዮን ቴል አቪቭ ከተማ አቅራቢያ እስራኤል የሚገኝ ዓለማቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ
ፎቶ ፋይል፦ ቤን ጉሪዮን ቴል አቪቭ ከተማ አቅራቢያ እስራኤል የሚገኝ ዓለማቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ

በአዲስ መልክ እየተዛመተ የሚገኘውን አዲሱ ዓይነት የኮሮናቫይረስ ዝርያ ወደ ሀገሯ እንዳይገባ እስራኤል በዚህ ሳምንት መጨረሻ ዓለማቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያዎቿን ልትዘጋ መሆኑን አስታውቃለች።

የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቤንጃሚን ኔትንያሁ እሁድ ዕለት እንደተናገሩት አዲሱን የቫይረስ ዝርያ ለመከላከልና የክትባት ዘመቻው በደንብ መሻሻል እስኪያሳይ ለአንዳንድ አስፈላጊ ጉዳዮች ካልሆነ በስተቀር የአየር መንገዶቹ ዝግ ይሆናሉ።

ይህ ውሳኔ በመጪው ማክሰኞ ጀምሮ ለአንድ ወር እንዲቆይ የታቀደ ሲሆን ለተግባራዊነቱ የፓርላማው ውሳኔ እየተጠበቀ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዩናይትድ ስቴትስ የዋይት ሀውስ ቤተመንግሥት እሁድ ዕለት ባወጣው መግለጫ ከደቡብ አፍሪካ የሚነሱ የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ተጓዦች እንዳይገቡ ለመከልከል መዘጋጀቱን አስታውቋል። ውሳኔው የተላለፈው ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በታየው አዲሱ ዓይነት የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ምክንያት ነው።

የዩናይትድ ስቴትስ የጤና ባለሞያዎች እንዳስታወቁት ሃገሪቱ አዳዲስ እየወጡ ያሉ የኮሮናቫይረስ ዝርያዎችን ለመከታተል ጥረት እያደረገች ሲሆን አላማውም አዳዲሶቹ ዝርያዎች እየተሰጡ ባሉ ክትባቶች ላይ ያላቸውን ተፅኖም ለመቆጣጠር መሆኑን የዩናይትድ ስቴትስ የበሽታዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ማዕከል ኃላፊ የሆኑት ሮቼል ዋልነስኪ አስታውቀዋል።

XS
SM
MD
LG