በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል 4ኛውን ዙር የኮቪድ ክትባት ዕድሜያቸው ከ60 በላይ ለሆኑትና የጤና ሠራተኞች ልትሰጥ ነው


የጤና ባለሞያዋ አራተኛውን የኮቪድ ክትባት ለመከተብ እየተሰናዱ፣ እስራኤል
የጤና ባለሞያዋ አራተኛውን የኮቪድ ክትባት ለመከተብ እየተሰናዱ፣ እስራኤል

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ናፍታሊ ቤነት ትናንት እሁድ በሰጡት መግለጫ እስራኤል አራተኛውን ዙር የኮቪድ-19 ክትባት መድሃኒት ዕድሜያቸው ከ60 በላይ ለሆኑና ለኦሚክሮን ቫይረሰ ሊጋለጡ ለሚችሉ የጤናው ዘርፍ ሠራተኞች እንድምትሰጥ አስታውቀዋል፡፡

የእስራኤል የህክምና ባለሙያዎች ሁለተኛውን የማጠናከሪያ ክትባት ባመረቱት ፋይዘር እና የባዮን ቴክ አምራቾች የተመረተውን አራተኛውን ዙሪ የማጠናከሪያ ክትባት የሰውነት መከላከል አቅማቸው ደካማ ለሆኑና በአረጋውያን መንከባከቢያ ስፍራዎች ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች እንዲሰጥ ባለፈው ሳምንት መወሰናቸው ይታወቃል፡፡

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር “እስራኤል አሁንም የዓለም አቀፉን የክትባት መርሃ ግብር ጥረት በመደገፉ ረገድ እንደገና ፈር ቀዳጅ ሆናለች” ብለዋል፡፡

እስራኤል ጤና ሚኒስቴር 9.4 ሚሊዮን ከሚሆን ህዝቧ መካከል 60 ከመቶ የሚሆኑት ሙሉውን ክትባት መውሰዳቸውን አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG