እስራኤል በጋዛ ከሐማስ ጋር በምታካሂደው ጦርነት ምክንያት ደቡብ አፍሪካ ያቀረበችውን የዘር ማጥፋት ክስ ለመቃወም ሄግ በሚገኘው አለም አቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት (ICJ) ፊት ትቀርባለች ሲሉ የእስራኤል መንግስት ቃል አቀባይ ዛሬ ማክሰኞ ተናግረዋል።
ደቡብ አፍሪካ፣ እስራኤል እ.ኤ.አ. በ1948 በወጣው የዘር ማጥፋት ተጠያቂነት ስምምነት የተጣለባትን ግዴታ በሐማስ ላይ በወሰደችው እርምጃ እየጣሰች መሆኗን በመግለጽ አስቸኳይ ትእዛዝ እንዲሰጥ ባለፈው ዓርብ ዓለም አቀፉን ፍርድ ቤት ጠይቃለች፡፡
ቃል አቀባዩ ኤይሎን ሌቪ "የእስራኤል መንግስት በሄግ በሚገኘው ዓለም አቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት የደቡብ አፍሪካን ስም ማጥፋት ለማጋለጥ ይቀርባል" ብለዋል።
"የደቡብ አፍሪካ መሪዎችን እናረጋግጥላቸዋለን ታሪክ ይፈርድባችኋል፣ ያለ ምህረትም ይፈርድባችኋል" ሲሉ ሌቪ አክለዋል፡፡
ደቡብ አፍሪቃ በእስራኤል በተያዙ ግዛቶች የፍልስጤምን የሀገርነት ጥያቄ ስትደግፍ ኖራለች።
በፍልስጤማውያን እየደረሰ ያለውን፣ በአፓርታይድ ዘመን በደቡብ አፍሪካ ከነበሩት አብዛኞቹ ጥቁሮች ችግር ጋር የምታመሳስላቸው ሲሆን እስራኤል ንጽጽሩን አጥብቃ ትቃወማለች።
የዓለም ፍርድ ቤት በመባል የሚታወቀው አይሲጄ (ICJ) በሀገሮች መካከል የሚነሱ አለመግባባቶችን ለመዳኘት የተቋቋመ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አካል ነው።
ደቡብ አፍሪካን የሚወክሉ ጠበቆች በታቀደው መሠረት ጉዳዩን በሚያዳምጠው ፍርድ ቤት ፊት እኤአ ጥር 11 እና 12 ለመቅረብ ዝግጅት እያደረጉ መሆኑ ተመልክቷል፡፡
የእስራኤልና ደቡብ አፍሪካ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በጋዛ ጦርነት ምክንያት ውጥረት የነገሠበት ሆኗል፡፡
ባላፈው ወር መጀመሪያ ላይ ደቡብ አፍሪካ በእስራኤል የነበራትን አምባሳደር ያስጠራች ሲሆን ሁሉንም ዲፕሎማቶቿን ማስወጣቷም ተዘግቧል፡፡
እስራኤል በጋዛ የተኩስ አቁም ለማድረግ እስከምትስማማ ድረስ፣ በአገሪቱ የሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ እንዲዘጋ እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዲቋረጥ የሚጠይቀውን የውሳኔ ሀሳብ በመደገፍ አብዛኞቹ የደቡብ አፍሪካ ህግ አውጭዎች ትናንት ማክሰኞ ድምጽ ሰጥተዋል።
የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ሀገራቸው “እስራኤል በሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን በተገደሉባት ጋዛ የጦር ወንጀሎችን እየፈፀመች እንደሆነ ታምናለች።” ሲሉ ከዚህ ቀደም በሰጡት መግለጫ መናገራቸውም በአሶሴይትድ ፕሬስ ዘገባ ተጠቅሷል፡፡
የሀገሪቱ ካቢኔም፣ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ነታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ እንዲያወጣ ዓለም አቀፉን የወንጀል ፍርድ ቤት መጠየቁ ተዘግቧል።
ባላፈው ወር መጀመሪያ ላይ ደቡብ አፍሪካ በእስራኤል የነበራትን አምባሳደር ያስጠራች ሲሆን ሁሉንም ዲፕሎማቶቿን ማስወጣቷም ተዘግቧል፡፡
የእስራኤል የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ በደቡብ አፍሪካ አምባሳደር የሆኑትን ኤልያቭ ቤሎቴርኮቭስኪን “ለምክክር” በሚል ወደ እየሩሳሌም የጠራ ሲሆን የእስራኤል መንግሥትም በደቡብ አፍሪካ የቀረበውን ክስ አስተባብሏል፡፡
የስራኤል ቃል አቀባዩ ኤይሎን ሌቪ እስራኤል የሰላማዊ ሰዎችን ሞት ለመቀነስ ጠንከር ያሉ እምርጃዎች መወሰዱንም ሌቪ ተናግረዋል፡፡
ሌቪ አያይዘውም “ለጀመረው ጦርነት፣ ከሆስፒታሎች ትምህር ቤቶች መስጊዶች፣ መኖሪያ ቤቶችና የተባበሩት ድርጅት ተቋማት ውስጥ ሆኖ ለሚያካሂዳቸው ጦርነቶች ሙሉ ኃላፊነት መውሰድ ያለበት ሐማስ ነው ብለዋል፡፡
መድረክ / ፎረም