በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል ዜጎቿ ወደ ቱርክ እንዳይሄዱ አስጠነቀቀች


ኢስታንቡል፣ ቱርክ እአአ ሰኔ 10/2022
ኢስታንቡል፣ ቱርክ እአአ ሰኔ 10/2022

ኢራን ወደ ቱርክ ለጉብኝት የሚሄዱ እስራኤላዊ ጎብኚዎችን ልትገል ወይም ልታግት ትችላለች በማለት እስራኤል ዜጎቿ ወደ ኢስታምቡል እንዳይጓዙ፣ እዛ የሚገኙትም በአስቸኳይ እንዲመለሱ ስትል የጉዞ ማስጠንቀቂያ አውጥታለች።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያኢር ላፒድ የእስራኤል የፀጥታ ሰራተኞች አደረጉት ባሉት "ከፍተኛ ጥረት" ባለፉት ሳምንታት የእስራኤላዊያንን ህይወት ማትረፋቸውን በመግለፅ የቱርክ መንግሥት ላበረከተው አስተዋፅኦም አመስግነዋል። በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃ ግን አልሰጡም።

አንድ የእስራኤል የደግንነት ባለሙያ ግን ለሮይተርስ ሲናገሩ ቱርክ የኢራን በርካታ አብዮት ጥበቃ አባላት የሆኑ የተወሰኑ ተጠርጣሪዎችን ማስሯን ገልፀዋል።

ላፒድ በቴሌቭዥን በሰጡት መግለጫም ሽብርተኞቹ በጉብኝት ላይ ያሉ እስራኤላዊያንን ኢላማ ማድረጋቸውን ገልፀው ፍላጎታቸው እስራኤላውያንን ለማገት ወይም ለመግደል ነው ብለዋል።

ግንቦት 14 ለተገደሉት የኢራን አብዮታዊ ጥበቃ አባል፣ ሀሰን ሳይድ ኮዳኢ እስራኤልን ተጠያቂ ያደረገችው ታህራል በእስራኤል ላይ የአፀፋ እርምጃ እንደምትወስድ አስታውቃ ነበር። እስራኤል ለቀረበባት ክስ የማረጋገጫም ሆነ የማስተባበያ ምላሽ ያልሰጠች ሲሆን ኮዳኢ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ዜጎቿ ላይ ጥቃት ለማድረስ እያሴረ ነው ስትል ግን ከሳ ነበር።

XS
SM
MD
LG