በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለተገደለው ኤርትራዊ መታሰቢያ የሻማ ሥነ-ሥርዓት ተካሄደ

እሥራኤል ቤርሣቤህ ከተማ ውስጥ ባለፈው ዕሁድ ለተገደለው ኤርትራዊ ስደተኛ ለወልደሚካዔል ዘርዖም መታሰቢያ ቴል አቪቭ ከተማ ውስጥ በሃገሩ ጊዜ ከምሽቱ አንድ እስከ ሦስት ሰዓት ሻማ የማብራት ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል።

ለተገደለው ኤርትራዊ መታሰቢያ የሻማ ሥነ-ሥርዓት ተካሄደ /ርዝመት፡-1ደ04ሰ/
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:04 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

እሥራኤል ቤርሣቤህ ከተማ ውስጥ ባለፈው ዕሁድ ለተገደለው ኤርትራዊ ስደተኛ ለወልደሚካዔል ዘርዖም መታሰቢያ ቴል አቪቭ ከተማ ውስጥ በሃገሩ ጊዜ ከምሽቱ አንድ እስከ ሦስት ሰዓት ሻማ የማብራት ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል።

እሥራኤል ውስጥ ለተገደለው ኤርትራዊ ወልደሚካዔል ዘርዖም ቴል አቪቭ ከተማ የተካሄደ ሻማ የማብራት ሥነ-ሥርዓት
እሥራኤል ውስጥ ለተገደለው ኤርትራዊ ወልደሚካዔል ዘርዖም ቴል አቪቭ ከተማ የተካሄደ ሻማ የማብራት ሥነ-ሥርዓት

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ አምስት ሺህ የሚሆን ሰው መገኘቱን ከተሣታፊዎቹ አንዱ አቶ ዖስማን ጣሃ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

ከዚህ በፊትም ብዙ ሥቃይ ማሣለፋቸውን የተናገሩት አቶ ዖስማን ከወልደሚካዔል መገደል ጋር ተያይዞ የወጡት መግለጫዎች አድራጎቱ የተፈፀመው በስህተት እንደሆነ ቢናገሩም ብዙ የተደራረቡ በደሎች እንደሚፈፀሙባቸው አመልክተዋል፡፡

“በትዕግስት እንወጣዋለን ብለን ግን እያለፍነው ነው፤ ባጠቃላይ እዚህ እሥራኤል ውስጥ ያለው ሕዝብ አማራጭ ስለሌለው እያለቀሰ ነው የሚገኘው” ብለዋል አቶ ዖስማን።

አቶ ዖስማን ጣሃ የተናገሩትን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG