በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል የቴሕራንን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ቅመማ ዕቅድ ማስወጣቷ ተገለፀ

FILE - An Iranian technician walks through the Uranium Conversion Facility just outside the city of Isfahan, south of the capital Tehran.
FILE - An Iranian technician walks through the Uranium Conversion Facility just outside the city of Isfahan, south of the capital Tehran.

ከአንድ የኢራን የመንግስት መጋዘን ሰብረው የገቡ የእስራኤል የጸጥታ ሠራተኞች በአሥር ሺዎች ገጾች የሚገመቱ የቴሕራንን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ቅመማ ዕቅድ የሚያመለክቱ ሰነዶችና እና ቁጥራቸው ሁለት መቶ የሚጠጋ የኮምፒውተር ዲስኮችን አሾልከው ማውጣታቸውን ታዋቂ የመገናኛ ብዙኃን ምንጮች ጠቆሙ።

ከአንድ የኢራን የመንግስት መጋዘን ሰብረው የገቡ የእስራኤል የጸጥታ ሠራተኞች በአሥር ሺዎች ገጾች የሚገመቱ የቴሕራንን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ቅመማ ዕቅድ የሚያመለክቱ ሰነዶችና እና ቁጥራቸው ሁለት መቶ የሚጠጋ የኮምፒውተር ዲስኮችን አሾልከው ማውጣታቸውን ታዋቂ የመገናኛ ብዙኃን ምንጮች ጠቆሙ።

የኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ በእሁድ እትሙ፡- “የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንጃሚን ኔታናያሁ የተባሉትን ሰነዶች የዩናይትድ ስቴትሱን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2015 ዓም በቴሕራን የኒውክሌር ቅመማ ፕሮግራም ዙሪያ ከኢራን ጋር ተደርሶ ከነበረው ስምምነት አገራቸውን እንዲያስወጡ ተጠቅመውበታል” ሲል ጽፏል።

ኒታንያሁ በተጨማሪም “ቴሕራን ወደፊት የአቶሚክ ቦምብ የመሥራት ፍላጎት አላት” ሲሉ ተከራክረዋል።

የብሪታንያው 'The Times' ጋዜጣ በበኩሉ ለንባብ ባበቃው ሌላ ዘገባ ሦሥት የዩናይትድ ስቴትስ ዘጋቢዎች ባለፈው ሳምንት በእስራኤል መንግስት ጋባዥነት ሰነዶቹን መመርመራቸውን አመልክቷል። ጋዜጣው አክሎም ኢራን የኒውክሌር ቅመማ ፕሮግራሟ “ለሰላማዊ ዓላማ ብቻ የታለመ ነው” ስትል አጥብቃ ብትከራከርም የምንግዜም ዓላማዋ ግን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ መሥራት ይመስላል፤ ብሏል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG