እኤአ ጥቅምት 7 በሀማስ ታጣቂዎች ከተገደሉት በተጨማሪ የሶስት ታጋቾች አስከሬን በጋዛ መገኘቱን የእስራኤል ጦር ዛሬ ዓርብ አስታወቀ፡፡
ሟቾቹ ሃናን ያብሎንካ፣ ሚሼል ኒሰንባ እና ኦሪዮን ሄርናንዴዝ ሲሆኑ ቤተሰቦቻቸው እንዲያውቁ ተደርጓል።
ይህ የተገለጸው የተባበሩት መንግስታት ከፍተኛው ፍርድ ቤት እስራኤል ወታደራዊ ዘመቻዋን በማቆም ግዛቱን ለቃ መውጣት አለባት በሚለው ሀሳብ ላይ ውሳኔ ለመስጠት በዝግጅት ላይ እያለ ነው።
በጥቅምት 7 ጥቃት በሀማስ የሚመሩ ታጣቂዎች 1,200 የሚጠጉ አብዛኞቹ ሲቪሎች የሆኑ ሰዎችን ገድለዋል፣ ሌሎች 250 የሚጠጉ ሰዎችን ደግሞ አግተው ወስደዋል።
እስራኤል 100 የሚጠጉ ታጋቾች አሁንም በጋዛ ታስረው እንደሚገኙ፣ ከተጨማሪ 30 የሚጠጉ አስከሬኖች ጋር እንደሚገኙ ገልጻለች።
ይህን ጥቃት ተከትሎ እስራኤል ጦርነቱን በጋዛ የጀመረች ሲሆን እስካሁን በተካሄደው ጦርነት የጋዛ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንደገለጸው ቢያንስ 35,000 ፍልስጤማውያን ተገድለዋል፡፡ በግድያው ተዋጊዎችና ሲቪሎች ተለይተው አልተመለከቱም፡፡
ዩናይትድ ስቴትስ በጋዛ እየተባባሰ ባለው ሰብዓዊ ሁኔታ ምክንያት ለእስራኤል የምትሰጠው ድጋፍ እንደሚቀንስ ዝታለች፡፡
በካታር፣ በዩናይትድ ስቴትስ እና በግብፅ ሸምጋይነት እየተካሄደ ያለው ድርድር ብዙም መሻሻል አላሳየም፡፡
መድረክ / ፎረም