እስራኤል ደቡባዊ ጋዛ በምትገኘው ራፋ ላይ የከፈተችውን ጥቃት አስመልክቶ ‘ተጨማሪ የአስቸኳይ ጊዜ እርምጃዎችን እንዲወሰዱ’ ስትል ደቡብ አፍሪካ ለአለም አቀፉ የወንጀል ችሎት ያቀረበችውን ጥያቄ በመቃወም ተከራክራለች።
በኔዘርላንድስ የደቡብ አፍሪቃው አምባሳደር ቩሲሙዚ ማዶንሴላ ትላንት ሐሙስ ለዓለም አቀፉ ችሎት ዳኞች ባቀረቡት ጥያቄ እስራኤል “ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ እና በአፋጣኝ፣ ሙሉ በሙሉ ጦሯን ከመላው የጋዛ ሰርጥ እንድታስወጣ” ትዕዛዝ እንዲሰጡ ነው የጠየቀችው።
‘የአለም አቀፉ ፍርድ ቤት በሁለቱ ቀናት ውሎው ‘የዘር ማጥፋትን የሚመለከተውን እና በ1949 የጸደቀውን ስምምነት ጥሳለች’ በሚል እስራኤል በደቡብ አፍሪቃ የቀረበባትን ክስም ተመልክቷል።
መድረክ / ፎረም