እስራኤላዊ ለበርካታ ዓመታት ካሰረቻቸው ፍልስጥኤማውያን አንዱ በዛሬው ዕለት ተለቅቀዋል፡፡
ካሪም የኑስ እስራኤላዊ ወታደር አግተው በመግደል ወንጀል የተሰጣቸውን የአርባ ዓመታት እስራት ቅጣት ከፈጸሙ በኋላ በዛሬው እለት ተፈትተው መኖሪያ መንደራቸው አራ ሲገቡ በብዙ መቶዎች የተቆጠሩ ደጋፊዎቻቸው ተቀብለዋቸዋል፡፡
ዩኒስ የታሰሩት አቭራሃም ቦምበርግ የተባለ እስራኤላዊ ወታደር በ1983 በእስራኤል በተያዘው በጎላን ሃይጽ ገድለዋል ተብለው መሆኑ ተዘግቧል፡፡
የእስራኤል የአገር አስተዳደር ሚኒስትር አሪዬህ ዴሪ የዩኒስን መለቀቅ በተመለከተ በጻፉት ደብዳቤ፣
“ዩኑስ በሽብር ተግባራቸው ተምሳሌት ለሆኑ ሁሉ ጠንካራ መልዕክት ለማስተላለፍ ዜኘታቸውን መገፈፍ አለባቸው" ማለታቸው ተጠቅሷል፡፡
ዩኑስ “ለፍልስጥኤም መስዋዕትነት ከከፈሉት መካከል አንዱ በመሆኔ አኮራለሁ” ብለዋል፡፡
በተያያዘ ዜና የእስራኤል ወታደሮች በዌስት ባንክ አንድ ፍልስጣኤማዊ ታዳጊ ወጣት በጥይት መትተው መግደላቸውን የእስራኤል ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡