በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእሥራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ከፕሬዝዳንት ከባራክ ኦባማ ጋር ተገናኙ


ወጣ ገባው የታየበት ግንኙነት ያላቸው ሁለቱ መሪዎች ለመጨረሻ ጊዜ ተገናኝተው ከተወያዩ ከአንድ ዓመት በላይ ሆኗቸዋል።

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማና የእሥራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንጃሚን ነታንያሁ (Benjamin Netanyahu) በዛሬው እለት ዋሽንግተን ላይ ኦባማ “በእጅጉ አሳሳቢ እየሆነ የመጣ” ሲሉ በገለጹት የመካከለኛው ምሥራቅ የጸጥታ ሁኔታ ዙሪያ እየተነጋገሩ ነው።

ወጣ ገባው የታየበት ግንኙነት ያላቸው ሁለቱ መሪዎች ለመጨረሻ ጊዜ ተገናኝተው ከተወያዩ ከአንድ ዓመት በላይ ሆኗቸዋል። በሌላ በኩል ያሁኑ የNetanyahu የዋይት ሃውስ ጉብኝት ዩናይትድ ስቴትስና ሌሎች አምስት ኃያላን መንግስታት በቴሕራን የኒዩክሌር ቅምመማ ፕሮግራም ዙሪያ ከኢራን ጋር ስምምነት ካደረጉ ወዲህ የመጀመሪያው ነው።

ኬን ብረድሚየር (Ken Bredemeier) ያጠናቀረውን የዚህን አጭር ዘገባ ዝርዝር አሉላ ከበደ አቅርቦታል። የድምጽ ፋይሉን ያዳምጡ።

የእሥራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ከፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ጋር ተገናኙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:50 0:00

XS
SM
MD
LG