በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእስራኤል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የኔታኒያሁን ህግ ሻረ


ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ
ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ

የእስራኤል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የራሱን አንዳንድ ሥልጣኖች የሚገደበውንና ከፍተኛ ብሄራዊ ተቃውሞ የቀሰቀሰውን የጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ የቀኝ ክንፍ መንግሥት ያወጣውን ህግ ትናንት ሰኞ እኤአ ጥር 1 2024 ውድቅ አድርጎታል፡፡

ህጉ በኔታንያሁ በሃይማኖታዊ እና ብሄራዊ አጋሮቻቸው ጥምርነት የቀረበ ሲሆን ፣ በእስራኤል ውስጥ ከፍተኛ መቃቃርን የፈጠረ እንደነበር ተመልክቷል፡፡

በሀገሪቱ የዲሞክራሲ መርሆዎች ላይ ስጋት ይፈጥራል በሚል የምዕራባውያን አጋሮችን ያሳሰበ ሰፊ የዳኝነት ማሻሻያ አካል እንደነበርም ተነግሯል፡፡

የትናንቱ የፍርድ ቤት ውሳኔ፣ ሐማስ እኤአ ህዳር 7 በደቡብ እስራኤል ጥቃት ካደረሰበት ጊዜ ጀምሮ በጦርነት ዘገባዎች ተሞልታ በነበረችው እስራኤል ውስጥ ተመልሶ አብይ ዜና ሆኗል፡፡

በፍርድ ቤቱ ፊት የቀረበው አዲሱ ህግ ፣ የመንግስትን እና የሚኒስትሮችን ውሳኔ መሻር የሚያስችሉትን ሁሉንም የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ሥልጣኖች ብቻ ሳይሆን አንዱን ብቻ የሰረዘ እንደነበር ተመልክቷል፡፡

የተሰረዘው ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ “ምክንያታዊ አይደሉም” ብሎ የጠረጣቸውን የመንግሥት ውሳኔዎች ውድቅ የማድረግ ሥልጣኑን እንደነበር ተጠቅሷል፡፡

ከጠቅላይ ፍርድ ቤቱ 15 ዳኞች መካከል ስምንቱ ህጉ እንዲሻር ድምጽ መስጠታቸውን ፍርድ ቤቱ አስታውቋል።

አብዛኞቹ ዳኞች ህጉን ለመቃወም የወሰኑት የእስራኤልን ዲሞክራሲ በእጅጉ ስለሚጎዳ ነው ሲል ፍርድ ቤቱ በውሳኔው ማጠቃለያ አመልክቷል፡:

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG