በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእሥራኤል ምርጫ


ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ
ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ

እሥራኤል የፊታችን ሚያዝያ ውስጥ አጠቃላይ ምርጫ እንደምታካሂድና ክኔሴቷን ወይም የተወካዮች ምክር ቤቷን እንደምትበትን የጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ፓርቲ ዛሬ አስታወቀ።

እሥራኤል የፊታችን ሚያዝያ ውስጥ አጠቃላይ ምርጫ እንደምታካሂድና ክኔሴቷን ወይም የተወካዮች ምክር ቤቷን እንደምትበትን የጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ፓርቲ ዛሬ አስታወቀ።

በጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ የሚመራው ጥምረት በውስጥ መከፋፈል ተቀስፎ ለወራት የዘለቀ ሲሆን በሃማስ ከሚመራው ጋዛ ሮኬቶች ለሚወነጨፉ ሮኬቶች የመንግሥቱ ምላሽ ደካማ ነው በሚል የመከላከያ ሚኒስትሩ አቪግዶር ሊበርማን በቅርቡ ሥልጣናቸውን ለቅቀዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ ወታደራዊ ምልመላ ውስጥ መግባታቸው ሃይማኖት በመንግሥቱ ሥራዎች ውስጥ ጣልቃ እንዳይገባ በሚከለክለው ሃሣብ ውስጥ ጣልቃ እንድንገባ ያደርገናል የሚል ሥጋት ያላቸው አክራሪ አይሁድ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሊኩድ ፓርቲ ባወጣው እነርሱንም በሚያካትተው የወታደራዊ አገልግሎት ዕቅድ ላይ ነቀፋ እያሰሙ ናቸው።

አጠቃላይ ምርጫው ይካሄዳል ተብሎ ቀደም ሲል ታቅዶ የነበረው ለመጭው ኅዳር ቢሆንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግን በሰባት ወራት ቀድሞ እንዲካሄድ ወስነዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG