በትናንቱ የእስራኤል ብሄራዊ ምርጫ ድምጽ ሰጥተው ከሚወጡ መራጮች የተሰበሰበ አስተያየት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ናታኒያሁ የሚቀጥለውን መንግሥት ለመመስረት የሚያበቃቸውን ውጤት ሳያገኙ እንደማይቀር ይጠቁማል መባሉን ተከትሎ የእስራኤል ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር ያኢር ላፒድ “መጨረሻው የታወቀ ነገረ የለም” ሲሉ ለደጋፊዎቻቸው ተናግረዋል፡፡
“ዛሬ ምሽት ለሁለተኛው ቀን ሊራዘም ነው፡፡” ያሉት ላፒድ “የመጨረሻው የምርጫ ኮሮጆ እስኪቆጠር ድረስ፣ ምንም የሚያበቃ፣ ምንም የመጨረሻ የሆነ ነገር የለም፡፡ ትዕግስት ባይኖረን እንኳ፣ ለመጨረሻው ውጤት በትዕግስት እንጠባበቃለን፡፡” ብለዋል፡፡
የናታኒያሁ ሊኩድ ፓርቲ 31 መቀመጫዎችን በመያዝ በምክር ቤቱ ትልቁ እንደሚሆን ሲጠበቅ የላፒድ የሽ አቲድ ፓርቲ በአንጻሩ ከ22 እስከ 24 መቀመጫዎችን በማሸነፍ በሁለተኛነት እንደሚከተል ተነግሯል፡፡
ይህም ሆኖ ከማክሰኞው ምርጫ በኋላ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አሸናፊ ነኝ ብለው ባያውጁም ፓርቲያቸው በምክር ቤቱ አብላጫ መቀመጫ ለመያዝ በሚያስችለው ይዞታ ላይ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
“ይህን ልንግራችሁ እችላለሁ፣ በርግጥ የመጨረሻውን እርግጠኛ ውጤት መጠበቅ አለብን። ይሁን እንጂ አንድ ነገር ግልጽ ነው። መንገዳችን፣ የሊኩድ ፓርቲ የተጓዘበት መንገድ፣ ትክክለኝነቱን አረጋግጧል፡፡ 52 መቀመጫዎችን በተቆናጠጥንበት ባለፈው ምርጫ አንዳች ታላቅ ድል ከምንጎናጽፍበት እርከን መቃረባችንን ላስታውሳችሁ እወዳለሁ፡፡” ብለዋል።
የትላንቱ ምርጫ እስራኤል አራት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ለአምስተኛ ጊዜ ያካሄደችው ሲሆን፣ ሁሉም በአብዛኛው ያተኮሩት ናታኒያሁ የመምራት ብቃት አላቸው ወይ በሚለው ላይ ነው፡፡
በበርካታ የሙስና ወንጀሎች ተከሰው ፍርድ ቤት የቀረቡት ኔታንያሁ በደጋፊዎቻቸው ዓይን በሌለ ነገር በከንቱ የተወነጀሉ፣ በተቀናቃኞጫቸው ዘንድ ደግሞ እምነት የማይጣልባቸው እና የዲሞክራሲ ደንቃራ ተደርገው ነው።
በርካታ ድምጽ በማግኘት በምሽቱ ገዝፎ የታየው የቀኝ አክራሪው የፓርላማ አባል ኢትማር ቤን ግቪር ሃይማኖታዊ የጽዮናዊነት አቀንቃኝ ፓርቲ ሶስተኛውን እርከን መቆናጠጡ ነው።
ላፒድ በቤላ በኩል ኒታን ያሁን ወደ ተቃዋሚዎች መሪነት የቀየረው ጥምረት ዋና አውጠኝጣኝ ናቸው።