በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤላዊ ብሔርተኞች በእየሩሳሌም ዓመታዊ ሠልፋቸውን አደረጉ

በአሥር ሺሕ የሚቆጠሩ እስራኤላዊ ብሔርተኞች በእየሩሳሌም ፍልስጤማውያን በብዛት በሚኖሩበት አካባቢ ዓመታዊ ሠልፋቸውን አድርገዋል።
በአሥር ሺሕ የሚቆጠሩ እስራኤላዊ ብሔርተኞች በእየሩሳሌም ፍልስጤማውያን በብዛት በሚኖሩበት አካባቢ ዓመታዊ ሠልፋቸውን አድርገዋል።

በአሥር ሺሕ የሚቆጠሩ እስራኤላዊ ብሔርተኞች በእየሩሳሌም ፍልስጤማውያን በብዛት በሚኖሩበት አካባቢ ዓመታዊ ሠልፋቸውን አድርገዋል።

አንዳንዶቹ ሰልፈኞች “ሞት ለዓረቦች” ሲሉም ተደምጠዋል። በዓመታዊ ሰልፉ ላይ ዘር ተኮር ስድብና ድብድብም ይስተዋላል።

የእስራኤልና ሐማስ ጦርነት እየተካሄደ ባለበት ወቅት ፀጥ ብላ በከረመችው እየሩሳሌም፣ ዛሬ የተካሄደው ሰልፍ የተስፋፋ ግጭት እንዳያስከትል ተሰግቷል።

ከሶስት ዓመታት በፊት የተካሄደውን ተመሳሳይ ሰልፍ ተከትሎ፣ በጋዛ የ11 ቀናት ጦርነት ተካሂዷል።

“የእየሩሳሌም ቀን” በሚል የሚካሄደው ዓመታዊ ሰልፍ፣ እስራኤል ምሥራቅ እየሩሳሌምን የያዘችበትን ቀን ለማክበር ነው። በእ.አ.አ 1967 የተካሄደውን ጦርነት ተከትሎ እስራኤል በአይሁዶች፣ በክርስቲያኖች እና በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ ቅዱስ ተደርጋ የምትታየውን ምሥራቅ እየሩሳሌም ተቆጣጥራለች፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG