የእስራኤል ወታደሮች ዛሬ ዌስት ባንክ ውስጥ ሦስት ፍልስጤማውያንን ገደሉ። ታጣቂዎቹ ናብለስ ከተማ ውስጥ ተሽከርካሪ ላይ ኾነው በእስራኤል ወታደሮች ላይ ተኩስ በከፈቱበት ወቅት መገደላቸውን የእስራኤል ጦር ሠራዊት በሰጠው ማብራሪያ አስታውቋል።
የእስራኤል ጦር ሠራዊት አክሎም ሦስት ጠመንጃ እና በርካታ ጥይቶች ከሌሎች ወታደራዊ ቁሳቁሶች ጋራ ከተሽከርካሪው ውስጥ ማግኘቱን አመልክቷል።
ጥቃቱ፤ እስራኤል የከፈተችውን ወታደራዊ ዘመቻ፣ የፍልስጤም ታጣቂዎች በፊናቸው የሚሰነዝሯቸውን ጥቃቶች እና እስራኤላውያን ሰፋሪዎች በፍልስጤም መንደሮች ላይ ያደረሱትን ጉዳት ጨምሮ በዌስት ባንክ ተባብሶ ከቀጠለው ብጥብጥ የቅርብ ጊዜው ነው።
መድረክ / ፎረም