በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል በዌስት ባንክ በከፈተችው ጥቃት 10 ሰዎች ሞቱ

የእስራኤል ጦር፣ በዌስት ባንክ የስደተኞች መጠለያ የሚያደርገውን አሠሣ፣ ለሁለተኛ ቀን በመቀጠል ላይ ባለበት በዛሬው ዕለት፣ የሟቾች ቁጥር ወደ 10 አሻቅቧል።

120 ተጠርጣሪ ታጣቂዎችን፣ መሣሪያዎችንና ፈንጂዎችን፣ ጀኒን ተብሎ ከሚጠራው መጠለያ እንደያዘ፣ ሠራዊቱ አስታውቋል።

የፍልስጥኤም የጤና ባለሥልጣናት፣ ትላንት ማምሻውን፥ የሁለት ተጨማሪ ሰዎች ሕይወት እንዳለፈ፣ ይህም፣ የሟቾቹን ቁጥር 10 እንዳደረሰው ተናግረዋል። ወደ 100 የሚጠጉ ጉዳተኞች መኖራቸውንም አስታውቀዋል።

እስራኤል፣ አሠሣውን፥ ትላንት ሰኞ ከጀመረች ወዲህ፣ ሦስት ሺሕ የሚኾኑ ሰዎችን ከካምፑ እንዳስወጣ፣ የፍልስጥኤም ቀይ ጨረቃ ማኅበር አስታውቋል።

እስራኤል የምታካሒደው አሠሣ፥ በድሮን ጥቃት፣ በቡልዶዘሮች፣ እንዲሁም በመቶ በሚቆጠሩ ወታደሮች እንደታገዘ ተመልክቷል።

ፍልስጥኤም፣ ጎረቤቶቿ ዮርዳኖስ እና ግብጽ፣ እንዲሁም 57 አገሮችን በአባልነት ያቀፈው የእስልምና ትብብር ድርጅት፣ ሁከቱን አውግዘዋል።

በዋሽንግተን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፥ ም/ቤቱ ግጭቱን በአንክሮ እየተከታተለ እንደኾነና የሰላማዊ ነዋሪዎች ሕይወት እንዳይጠፋ ጥንቃቄ እንዲወሰድ አሳስቧል።

XS
SM
MD
LG