በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእስራኤል ሠራዊት ሶስት ፍልስጤማውያንን ገደለ

ዌስት ባንክ ውስጥ በሚገኝ የስደተኞች ጣቢያ ላይ የእስራኤል ሠራዊት ባደረሰው ጥቃት 3 ፍልስጤማውያን መገደላቸውን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።
ዌስት ባንክ ውስጥ በሚገኝ የስደተኞች ጣቢያ ላይ የእስራኤል ሠራዊት ባደረሰው ጥቃት 3 ፍልስጤማውያን መገደላቸውን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

ዌስት ባንክ ውስጥ በሚገኝ የስደተኞች ጣቢያ ላይ የእስራኤል ሠራዊት ባደረሰው ጥቃት 3 ፍልስጤማውያን መገደላቸውን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

የፍልስጤም የጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው 6 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል። አንድ ተጎጂ በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ ይገኛል ተብሏል።

የእስራኤል ሰራዊት ሶስት ሰዎች መገደላቸውን አረጋግጦ፣ አባላቱ ላይ ተኩስ በመከፈቱ የአጸፋ ርምጃ ተወስዷል ብሏል።

በፍልስጤማውያን የሚፈጸመው ጥቃት እየጨመረ ነው በሚል፣ እስራኤል ላለፈው አንድ ዓመት አሰሳዋን አጠናክራለች፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የባይደን አስተዳደር ትናንት እሁድ ባወጣው መግለጫ፣ እስራኤል ዌስት ባንክ ላይ የምታካሂደውን ሰፈራ ነቅፏል። የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማቲው ሚለር “እስራኤል በተያዙት ግዛቶች ላይ የምታካሂደው ፖሊስ እጅግ አሳሳቢ” ነው ብለዋል።

እስራኤል 700 ሺሕ ሰዎችን በዌስት ባንክ ማስፈሯ ለሰላም እንቅፋት ነው ሲሉ በርካታ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ አባላት ይገልጻሉ።

ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጀምሮ እስራኤል ባደረሰችው ጥቃት ከ250 በላይ ፍልስጤማውያን ተገድለዋል። ፍልስጤማውያኑ በእስራኤላውያኑ ላይ ባደረሱት ጥቃት ደግሞ 50 ሰዎች ተገድለዋል።

XS
SM
MD
LG